እወድሃለሁ (Ewedehalehu) - ሃና ፡ ተክሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሃና ፡ ተክሌ
(Hana Tekle)

Hana Tekle 1.jpg


(1)

አግዘኝ
(Agezegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሃና ፡ ተክሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

 
በባዶነቴ ፡ አግኝተኀኛል
አንተ ፡ እኔን ፡ መውደድ ፡ ያስገርመኛል
አወዳደድህ ፡ ከመውደድ ፡ ያልፋል
ወደድኩህ ፡ ብልህ ፡ ምን ፡ ያስገርማል

ለምንድን ፡ ነው ፡ አልልህም
ስራህ ፡ ጠፍቶኝ ፡ አልጠይቅህም
የምልህ ፡ ግን ፡ አንድና ፡ ግልጽ ፡ ነው
ስለወደድከኝ ፡ ወድጄሃለሁ

አዝ:- እወድሃለሁ ፡ አሳብዬ
እወድሃለሁ (፪x)
ስለወደድከኝ ፡ አሳብዬ
ወድጄሃለሁ (፪x)
ወድጄሃለሁ ወድጄሃለሁ

ለመውደዴ ፡ ገደብ ፡ የለኝም
ምገልጸበት ፡ ቋንቋም ፡ አላገኝም
ብቻ ፡ ነፍሴ ፡ አፍቅራሃለች
እንደወደድካት ፡ ትወድሃለች

አዝ:- እወድሃለሁ ፡ አሳብዬ
እወድሃለሁ (፪x)
ስለወደድከኝ ፡ አሳብዬ
ወድጄሃለሁ (፪x)

የአንተ ፡ ፍቅር ፡ መውደድህ ፡ አያልቅም
መውደዴ ፡ ግን ፡ የአንተን ፡ ፍፁም ፡ አይገልጸውም
አይገልጸውም ፡ ብዬ ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁ
በትንሿ ፡ ልቤ ፡ አቅሜ ፡ ቢሆንም ፡ ይሄው ፡ እወድሃለሁ

አዝ:- እወድሃለሁ ፡ አሳብዬ
እወድሃለሁ (፪x)
ስለወደድከኝ ፡ አሳብዬ
ወድጄሃለሁ (፪x)

እወድሃለሁ (፫x)