አንለያይም (Aneleyayem) - ሃና ፡ ተክሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሃና ፡ ተክሌ
(Hana Tekle)

Hana Tekle 1.jpg


(1)

አግዘኝ
(Agezegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሃና ፡ ተክሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

 
ውጣ ፡ ውረድ ፡ ቢበዛ ፡ እንኳን ፡ ቢጨንቀኝም ፡ ማደርገዉ
አንተን ፡ ትቼ ፡ ሌላ ፡ አማራጭ ፡ መፈለግ ፡ አይሆንልኝም
ውላችን ፡ አይደለም ፡ ስኬት ፡ ሳይሆንልኝ ፡ ግን ፡ ልርቅህ
በደምህ ፡ የተዋጀሁት ፡ በቂዬ ፡ ነው ፡ ማንነትህ

አዝ:- የወደድከኝ ፡ ጌታ ፡ አከበርኩህ ፡ ጌታ
ነፍሴም ፡ ተሰጥታለች ፡ ለአንተ ፡ ታዚም ፡ ሁሌም ፡ ጠዋት ፡ ማታ
ቃልኪዳናችንም ፡ ዘለዓለማዊ ፡ ነው
አጋጣሚ ፡ አይደለምና ፡ ፍቅርህ ፡ ሁኔታ ፡ ላይ ፡ ያየሁህ
አንለያይም (፰x)

ሄድኩኝ ፡ ብለው ፡ ከሄዱበት ፡ አንዳች ፡ የለም ፡ የተረፈ
ዛሬ ፡ ታይቶ ፡ ከሚጠፋው ፡ ከዚች ፡ ምድር ፡ ያለፈ
ዛለዓለሜ ፡ ቤቴ ፡ የአንተ ፡ ይሁን ፡ ይህን ፡ እወዳለሁ
በከንፈሬ ፡ ሳልበድልህ ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ መርጫለሁ

አዝ:- የወደድከኝ ፡ ጌታ ፡ አከበርኩህ ፡ ጌታ
ነፍሴም ፡ ተሰጥታለች ፡ ለአንተ ፡ ታዚም ፡ ሁሌም ፡ ጠዋት ፡ ማታ
ቃልኪዳናችንም ፡ ዘለዓለማዊ ፡ ነው
አጋጣሚ ፡ አይደለምና ፡ ፍቅርህ ፡ ሁኔታ ፡ ላይ ፡ ያየሁህ
አንለያይም (፰x)

የአንተ ፡ ብሆን ፡ መታደሌ ፡ የጌታ ፡ ልጅ ፡ መባሌ
ተጠርቼ ፡ መች ፡ ቀረሁኝ ፡ አባ ፡ በአንተ ፡ ተወደድኩኝ
ምን ፡ አጥቼ ፡ ልሂድ ፡ ከአንተ ፡ ምን ፡ ጐድሎብኝስ ፡ ከእቅፍህ
የእኔ ፡ ብዬ ፡ ምኖርበት ፡ መመኪያዬም ፡ ጌጤም ፡ ቤትህ

አዝ:- የወደድከኝ ፡ ጌታ ፡ አከበርኩህ ፡ ጌታ
ነፍሴም ፡ ተሰጥታለች ፡ ለአንተ ፡ ታዚም ፡ ሁሌም ፡ ጠዋት ፡ ማታ
ቃልኪዳናችንም ፡ ዘለዓለማዊ ፡ ነው
አጋጣሚ ፡ አይደለምና ፡ ፍቅርህ ፡ ሁኔታ ፡ ላይ ፡ ያየሁህ
አንለያይም (፲፮x)