ይኽው (Yehiew) - ኃይለኢየሱስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኃይለኢየሱስ ፡ ታደሰ
(Haileyesuse Taddesse)

Haileyesuse Taddesse 1.jpg


(1)

አየሁ
(Ayehu)

ዓ.ም. (Year): ፳፻፮ (2013)
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኃይለኢየሱስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Haileyesuse Taddesse)

 
አሃ ፡ አሃ

አዝለድል ፡ እንጂ ፡ ለሽንፈት ፡ እኔ ፡ አልተጠራሁም (፪x)
ጌታዬ ፡ ሲጠራኝ ፡ ከዚያ ፡ ከጨለማ
እባብና ፡ ጊንጡን ፡ እንድረግጥ ፡ ነውና
እየሱስ ፡ ሲያወጣኝ ፡ ከዚያ ፡ ከጨለማ
እባብና ፡ ጊንጡን ፡ እንድረግጥ ፡ ነውና

በማይመች ፡ ነገር ፡ የሚመቸው ፡ ጌታ ፡ አሃሃ
ከእኔ ፡ ጋር ፡ ስላለ ፡ በድፍረት ፡ እላለሁ ፡ እየሱስ ፡ ነው ፡ ጌታ
(፪x)
ድል ፡ አድራጊዉ ፡ ጌታ ፡ ድል ፡ ያንተ ፡ ነዉ ፡ ብሏል
ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ስማ ፡ ድል ፡ መንሳትስ ፡ የታል
አሸናፊው ፡ ጌታ ፡ ድል ፡ ያንተ ፡ ነው ፡ ብሏል
ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ስማ ፡ ድል ፡ መንሳትስ ፡ የታል

አዝለድል ፡ እንጂ ፡ ለሽንፈት ፡ እኔ ፡ አልተጠራሁም (፪x)
ጌታዬ ፡ ሲጠራኝ ፡ ከዚያ ፡ ከጨለማ
እባብና ፡ ጊንጡን ፡ እንድረግጥ ፡ ነውና
እየሱስ ፡ ሲያወጣኝ ፡ ከዚያ ፡ ከጨለማ
እባብና ፡ ጊንጡን ፡ እንድረግጥ ፡ ነውና

የምሞትበት ፡ ተሽሯል ፡ አዋጁ
ትዕዛዝ ፡ አውጥቷል ፡ ታሪክን ፡ ለዋጩ
መስንቆዬም ፡ ይውረድ ፡ ከተሰቀለበት
ለአሸናፊው ፡ ጌታ ፡ መዝሙር ፡ ይዜምበት
በአዲስ ፡ ምስጋና ፡ በዕልልታ ፡ ሆታ
ፊቱ ፡ እገባለሁ ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ ጌታ ፡
ይኽው ፡ ሽብሸባ ፡ ይኽው ፡ ስግደቴ
ድልን ፡ ስለሰጠኝ ፡ ለመድሃኒቴ
ለሆነኝ ፡ ጉልበቴ ፡ ይኽው ፡ ስግደቴ
ይኽው ፡ እኔነቴ

አዝ፦ ይኽው ፡ ተቀበለው ፡ ጌታ
ይኽው ፡ ላንተ ፡ ያለኝ ፡ ዕልልታ
ይኽው ፡ ተቀበለው ፡ አባ
ይኽው ፡ ላንተ ፡ ያለኝ ፡ ጥብጨባ
ይኽው ፡ ይኽው ፡ አምልኮው ፡ ይኽው
ይኽው ፡ ይኽው ፡ ዝማሬዉ ፡ ይኽው
ይኽው ፡ ይኽው ፡ ሽብሸባው ፡ ይኽው
ይኽው ፡ ይኽው ፡ ዕልልታው ፡ ይኽው

ጨለማዬ ፡ በራ ፡ የፅድቅ ፡ ፀሃይ ፡ ወጣ
የመጐብኘት ፡ ዘመን ፡ ይኽው ፡ ለእኔ ፡ መጣ
እንዲሁ ፡ አልቀረሁም ፡ በመድረ ፡ በዳ ፡ ላይ
ዘንበለ ፡ ብሎልኛል ፡ ጌታዬ ፡ ከሰማይ
ስሙ ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ ይወደስ ፡ ይግነን
የአምልኮ ፡ ሽታ ፡ ቤቱን ፡ የሙላልኝ
በጠላቴ ፡ ላይ ፡ ድልን ፡ ለሰጠኝ ፡ ለዚህ ፡ ለጌታ
እልልታ ፡ አለኝ ፡ ዝማሬ ፡ አለኝ
ሽብሸባ ፡ አለኝ ፡ አምልኮ ፡ አለኝ

አዝ፦ ይኽው ፡ ተቀበለው ፡ ጌታ
ይኽው ፡ ላንተ ፡ ያለኝ ፡ ዕልልታ
ይኽው ፡ ተቀበለው ፡ አባ
ይኽው ፡ ላንተ ፡ ያለኝ ፡ ጥብጨባ
ይኽው ፡ ይኽው ፡ አምልኮው ፡ ይኽው
ይኽው ፡ ይኽው ፡ ዝማሬዉ ፡ ይኽው
ይኽው ፡ ይኽው ፡ ሽብሸባው ፡ ይኽው
ይኽው ፡ ይኽው ፡ ዕልልታው ፡ ይኽው