From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ትመቸኛለህ ፡ ጌታዬ
ትመቸኛለህ ፡ ኢየሱስ (፪x)
ከእናት ፡ ማህፀን ፡ እስከ ፡ ሽመግልና ፡ ድረስ
ምተሸከም ፡ አምላክ ፡ ቃልህን ፡ ማታፈርስ
ፍፁም ፡ ነው ፡ ፍቅርህ ፡ የሱስ ፡ ያለ ፡ እንከን ፡ የሆነ
የኽው ፡ ተስፋ ፡ ያለው ፡ ሠው ፡ አረከኝ ፡ ህይወቴ ፡ ሰከነ (፪x)
አዝ፦ ትመቸኛለህ ፡ ጌታዬ
ትመቸኛለህ ፡ ኢየሱስ (፬x)
በዓለም ፡ ሣለሁኝ ፡ ከአለም ፡ ተለይቼ ፡ ልኖር
ከንቱ ፡ እንደሆነ ፡ አውቄ ፡ የዚህች ፡ ምድር ፡ ክብር
ስደክም ፡ ስበረታ ፡ በህይወት ፡ መንገድ ፡ ላይ
ክንዶች ፡ ያሣረፈኝ ፡ የደላኝ ፡ የለም ፡ ካንተ ፡ በላይ
አዝ፦ ትመቸኛለህ ፡ ጌታዬ
ትመቸኛለህ ፡ ኢየሱስ (፬x)
ሳልወድ ፡ ወይም ፡ ሣልሮጥ ፡ ምህረትን ፡ አግኝቻለሁ
ነፍሴን ፡ አርክተሀት ፡ ልዩ ፡ ሰው ፡ ሆኜአለሁ
መቅበዝበዜ ፡ አሣዝኖህ ፡ ፈልገህ ፡ አግኝተኽኝ
ከቶ ፡ እንዳይጠማኝ ፡ የሕይወትን ፡ ውሃ ፡ አጠጣኽኝ
አዝ፦ ትመቸኛለህ ፡ ጌታዬ
ትመቸኛለህ ፡ ኢየሱስ (፬x)
የልቤ ፡ ፍሰሀ ፡ አምላኬና ፡ አባቴ ፡ ለኔ
መቼም ፡ የማትተወኝ ፡ ማገኝህ ፡ ከጐኔ
ምላሴ ፡ ሲያከብርህ ፡ በሚችለው ፡ ሁሉ
የአካል ፡ ክፍሎቼ ፡ ተባብረው ፡ በደስታ ፡ ያመልካሉ
አዝ፦ ትመቸኛለህ ፡ ጌታዬ
ትመቸኛለህ ፡ ኢየሱስ (፰x)
|