ስለ ፡ አምላክነትህ (Seleamlakeneteh) - ኃይለኢየሱስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኃይለኢየሱስ ፡ ታደሰ
(Haileyesuse Taddesse)

Haileyesuse Taddesse 1.jpg


(1)

አየሁ
(Ayehu)

ዓ.ም. (Year): ፳፻፮ (2013)
ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኃይለኢየሱስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Haileyesuse Taddesse)

 
አዝ፦ ስለ ፡ አምላክነትህ ፡ ስለ ፡ ጌትነትህ
ስለ ፡ እጆችህ ፡ ስራ ፡ ባወራው ፡ ባወራ
አያልቅ ፡ የአንተ ፡ ሥራ (፪x)
አያልቅ ፡ የአንተ ፡ ስራ (፬x)

ሰባቱን ፡ ከዋክብት ፡ ኦርዬንን ፡ የሰራ
ጨለማውን ፡ ንጋት ፡ ብርሀን ፡ የሚያበራ
ቀኑን ፡ አጨልሞ ፡ ሌሊት ፡ የሚያደርገው
ስራው ፡ እንዲህ ፡ ያማረው ፡ ስሙ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነዉ
(፪x)

አዝ፦ ስለ ፡ አምላክነትህ ፡ ስለ ፡ ጌትነትህ
ስለ ፡ እጆችህ ፡ ስራ ፡ ባወራው ፡ ባወራ
አያልቅ ፡ የአንተ ፡ ሥራ (፪x)
አያልቅ ፡ የአንተ ፡ ስራ (፬x)

ውሆችን ፡ በእፍኙ ፡ የሰፈረ ፡ ጌታ
ሰማይንም ፡ ደግም ፡ በስንዝር ፡ የለካ
ኽረ ፡ እግዚአብሔርን ፡ የአማከረው ፡ ማነው
ማስተዋሉ ፡ ረቂቅ ፡ ኃይሉ ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው
(፪x)

አዝ፦ ስለ ፡ አምላክነትህ ፡ ስለ ፡ ጌትነትህ
ስለ ፡ እጆችህ ፡ ስራ ፡ ባወራው ፡ ባወራ
አያልቅ ፡ የአንተ ፡ ሥራ (፪x)
አያልቅ ፡ የአንተ ፡ ስራ (፬x)

በዓመታት ፡ መሀል ፡ ስራን ፡ ትሰራለህ
ሁኔታ ፡ አያግድህ ፡ ከሁኔታ ፡ በላይ ፡ ነህ
አቤት ፡ ይሄ ፡ ጌታ ፡ እኔ ፡ የማመልከው
ለዘላለም ፡ ነዋሪ ፡ መለወጥ ፡ የማያውቁው
(፪x)

ስለዚህ ፡ ላምልከው ፡ በሀሴት ፡ ውሰጥ ፡ ሆኜ
የማይለወጠውን ፡ ስላገኘች ፡ ነፍሴ
ከቤቱ ፡ በረከት ፡ ስለረካች ፡ ነፍሴ (፪x)

ከእርሱ ፡ ሌላ ፡ አልፈልግም
እርሱ ፡ ለእኔ ፡ ምኞቴ ፡ ነው
ርሀቤም ፡ ጥማቴም ፡ የሆነው
ከእርሱ ፡ ሌላ ፡ አልፈልግም
እርሱ ፡ ለእኔ ፡ መሻቴ ፡ ነው
ርሀቤም ፡ ጥማቴም ፡ የሆነው
ርሀቤም ፡ ጥማቴም ፡ የሆነው (፲፮x)