From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
በመንገድህ ፡ አግኘኝ ፡ ጌታ ፡ እንደ ፡ ሀሳብህ
ለትጐበኘኝ ፡ ስትመጣ ፡ እንዳልጠፋ ፡ ከፊትህ
ፀጋህን ፡ አብዛልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ በሕይወቴ
መንፈስህ ፡ ያግዘኝ ፡ ይጽና ፡ መሰረቴ (፪x)
አዝ፦ ምህረትን ፡ ትወዳለህና
ብርታትን ፡ ትሰጣለህና
እኔም ፡ ልታሰብ ፡ ጌታ
ኃይል ፡ ይብዛልኝ ፡ ልበርታ
ኑሮዬ ፡ አንተን ፡ ይምሰልህ
ከፍ ፡ ያድርግህ ፡ ያክብርህ ፡ አሜን
ስለ ፡ እኔ ፡ ነፍስህን ፡ ልትሰጥ ፡ አልሰሰትክምና
እዳዬን ፡ ሁሉ ፡ ልትከፍል ፡ ተችሎሀልና
እኔም ፡ ለመውደድህ ፡ ልሁን ፡ እንደልብህ
አንተን ፡ መፍራት ፡ ሙላኝ ፡ ዝቅ ፡ ልበልልህ (፪x)
አዝ፦ ምህረትን ፡ ትወዳለህና
ብርታትን ፡ ትሰጣለህና
እኔም ፡ ልታሰብ ፡ ጌታ
ኃይል ፡ ይብዛልኝ ፡ ልበርታ
ኑሮዬ ፡ አንተን ፡ ይምሰልህ
ከፍ ፡ ያድርግህ ፡ ያክብርህ ፡ አሜን
በመቅደስህ ፡ ቀድሰኝ ፡ በእሣትህ ፡ አንጥረኝ
የማትወደው ፡ ከእኔ ፡ ይቆረጥ ፡ እንዳሻህ ፡ አበጃጀኝ
ለእኔም ፡ የሻለኛል ፡ በእጅህ ፡ መቀረፁ
ኋላ ፡ ሞልቶ ፡ ይፈሣል ፡ ከአንተ ፡ በረከቱ (፪x)
አዝ፦ ምህረትን ፡ ትወዳለህና
ብርታትን ፡ ትሰጣለህና
እኔም ፡ ልታሰብ ፡ ጌታ
ኃይል ፡ ይብዛልኝ ፡ ልበርታ
ኑሮዬ ፡ አንተን ፡ ይምሰልህ
ከፍ ፡ ያድርግህ ፡ ያክብርህ ፡ አሜን
ድንጋዩ ፡ ልብ ፡ ከእኔ ፡ ይውጣ ፡ ስጋ ፡ ይሁንልኝ
የቀናውን ፡ መንፈስህን ፡ በውስጤ ፡ አድስልኝ
ክርስቲያን ፡ ከተባልኩ ፡ በአንተ ፡ ከተጠራሁ
እንደ ፡ ሀሳብህ ፡ ኖሬ ፡ ማለፍን ፡ እሻለሁ (፪x)
አዝ፦ ምህረትን ፡ ትወዳለህና
ብርታትን ፡ ትሰጣለህና
እኔም ፡ ልታሰብ ፡ ጌታ
ኃይል ፡ ይብዛልኝ ፡ ልበርታ
ኑሮዬ ፡ አንተን ፡ ይምሰልህ
ከፍ ፡ ያድርግህ ፡ ያክብርህ ፡ አሜን (፪x)
|