ማረኝ (Maregn) - ኃይለኢየሱስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኃይለኢየሱስ ፡ ታደሰ
(Haileyesuse Taddesse)

Haileyesuse Taddesse 1.jpg


(1)

አየሁ
(Ayehu)

ዓ.ም. (Year): ፳፻፮ (2013)
ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኃይለኢየሱስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Haileyesuse Taddesse)

 
እጅህ ፡ አላጠረም ፡ ከመስራት
ድምጽህ ፡ አልደከምም ፡ ከመጥራት
ይልቅ ፡ በበደሌ ፡ ያሳዘንኩህ ፡ እኔ
ማስተዋል ፡ ያቃተኝ ፡ በቃልህ ፡ ስትነግረኝ
ስለዚህ ፡ አምልኮዬ ፡ ሆነ ፡ አንካሳ
አንዳች ፡ ጠብ ፡ አይልም ፡ በስምህ ፡ ብወቅድ ፡ ብነሳ

አዝማረኝ ፡ ማረኝ ፡ ጌታ ፡ ማረኝ (፪x)
ማረኝ ፡ ማረኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ማረኝ

የእኔ ፡ ነው ፡ ጠብና ፡ ክርክር
ከአንተ ፡ ይልቅ ፡ መፈለግ ፡ የራስ ፡ ክብር
የተጋረደ ፡ ነው ፡ በእኔ ፡ ያለው ፡ ብርሀን
እንቅፋት ፡ ሆኛለሁ ፡ ስለ ፡ ሌሎች ፡ መዳን
ኑሮዬ ፡ ምልክት ፡ የለውም ፡ የአንተነት
ሥጋዬ ፡ በርትቶአል ፡ መንፈሴ ፡ ግን ፡ ደክሟል

አዝማረኝ ፡ ማረኝ ፡ ጌታ ፡ ማረኝ (፪x)
ማረኝ ፡ ማረኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ማረኝ

አይታዘዝ ፡ ልቤ ፡ ጠማማ
ምላሴ ፡ አይደንግጥ ፡ ሲያማ
ወገኑን ፡ የማይወድ ፡ ቂመኛ ፡ ልብ ፡ ያለው
ትዕቢት ፡ የተሞላ ፡ ከኔ ፡ ሌላ ፡ ማነው
የቀደሙወን ፡ ፍቅር ፡ ከጣልኩት ፡ በጣም ፡ ቆይቻለሁ
ሰው ፡ ሲያየኝ ፡ የቆምኩኝ ፡ ብመስልም ፡ እኔስ ፡ ወድቂያለሁ

አዝማረኝ ፡ ማረኝ ፡ ጌታ ፡ ማረኝ (፪x)
ማረኝ ፡ ማረኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ማረኝ

ሁለንተናዬ ፡ ግልጽ ፡ በፊትህ
አንዳች ፡ እንኳን ፡ የለ ፡ ማልነግርህ
ከእግርህ ፡ ስር ፡ ወድቃለሁ ፡ እስከነህ ፡ ኃጢያቴ
በደምህ ፡ ታመኜ ፡ ዳግም ፡ ለመንፃቴ
እባህክ ፡ ስለ ፡ ስምህ ፡ ብለህ ፡ ራራልኝ
በቀራንዮ ፡ መስቀል ፡ በከፈልከው ፡ ዋጋ ፡ አስበኝ

አዝማረኝ ፡ ማረኝ ፡ ጌታ ፡ ማረኝ (፪x)
ማረኝ ፡ ማረኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ማረኝ

አንደገና ፡ እንደ ፡ አዲስ ፡ ሃይልን ፡ እሞላለሁ
አዝ፡- በንስሀ ፡ ፍሬያማ ፡ ህይወት ፡ እኖራለሁ
ፀጋህ ፡ ይበዛለኛል ፡ ቃልህ ፡ እበላለሁ
መንፈስህን ፡ ጠጥቼ ፡ የልብህ ፡ ሰው ፡ እሆናለሁ