ላመስግንህ (Lamesgeneh) - ኃይለኢየሱስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኃይለኢየሱስ ፡ ታደሰ
(Haileyesuse Taddesse)

Haileyesuse Taddesse 1.jpg


(1)

አየሁ
(Ayehu)

ዓ.ም. (Year): ፳፻፮ (2013)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኃይለኢየሱስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Haileyesuse Taddesse)

 
የህይወቴ ፡ እስትንፋስ ፡ በእጅህ ፡ መዳፍ ፡ ውስጥ ፡ ነው ፡ ያለው
ያለ ፡ አንተ ፡ መኖር ፡ አልችልም ፡ በእርግጥ ፡ ሞቼ ፡ እቀራለሁ
ህያውነቴ ፡ ባንተ ፡ ነው ፡ በነፍሴ ፡ ጌታ
ለዘላለም ፡ ላመስግንህ ፡ ላዚም ፡ በእልልታ
(፪x)
ልባርክህ ፡ ልባርክህ
ላምልክህ ፡ ላምልክህ (፪x)

አዝበአዲስ ፡ በአዲስ ፡ ቅኔ ፡ እቀኝልሀለሁ ፡ እኔ
በአዲስ ፡ በአዲስ ፡ ዜማ ፡ ድምጼ ፡ ለአንተ ፡ ይሰማ
(፪x)
ከልቤ ፡ በሙሉ ፡ ሀይሌ (፪x)
አመሰግንሀለሁ ፡ ክብርን ፡ ለአንተ ፡ እሰጣለሁ (፪x)
ኢየሱስ (፪x)
ኢየሱስ (፬x)

አምላኬ ፡ አንተ ፡ ለእኔ ፡ መታመኛዬ ፡ አለቴ
ደስታዬ ፡ አንተን ፡ ሳስብ ፡ ነው ፡ በእርግጥ ፡ ማረፍ ፡ መርካቴ
ስለዚህ ፡ አንተን ፡ ላምልክህ ፡ ላውራ ፡ ክብርህን
የዝማሬ ፡ ጽምፅ ፡ ይሰማ ፡ ላሸብሽብልህ
(፪x)
ከፍ ፡ ላርግህ ፡ ከፍ ፡ ላርግህ
ላውድስህ ፡ ላወድስህ (፪x)

አዝበአዲስ ፡ በአዲስ ፡ ቅኔ ፡ እቀኝልሀለሁ ፡ እኔ
በአዲስ ፡ በአዲስ ፡ ዜማ ፡ ድምጼ ፡ ለአንተ ፡ ይሰማ
(፪x)
ከልቤ ፡ በሙሉ ፡ ሀይሌ (፪x)
አመሰግንሀለሁ ፡ ክብርን ፡ ለአንተ ፡ እሰጣለሁ (፪x)
ኢየሱስ (፪x)
ኢየሱስ (፬x)

እንዳንተ ፡ የሚሆን ፡ ለእኔ ፡ አላገኘሁምና
ከእናትም ፡ ከአባት ፡ ከወዳጅ ፡ በልጠህብኛልና
አምላኬ ፡ መድሀኒቴ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ፈዋሼ
በአምላኮ ፡ አንተን ፡ ማክበር ፡ ነው ፡ ምላሼ
(፪x)
ላመስግንህ ፡ ላመስግንህ
ላሞጋግስህ ፡ ላሞጋግስህ (፪x)

አዝበአዲስ ፡ በአዲስ ፡ ቅኔ ፡ እቀኝልሀለሁ ፡ እኔ
በአዲስ ፡ በአዲስ ፡ ዜማ ፡ ድምጼ ፡ ለአንተ ፡ ይሰማ
(፪x)
ከልቤ ፡ በሙሉ ፡ ሀይሌ (፪x)
አመሰግንሀለሁ ፡ ክብርን ፡ ለአንተ ፡ እሰጣለሁ (፪x)
ኢየሱስ (፪x)

ማፍቀሬን ፡ ለአንተ ፡ ያለኝን ፡ ጥልቅ ፡ የሆነ ፡ መውደዴን
እገልፃለሁ ፡ ለስምህ ፡ ክብር ፡ በማቅረብ ፡ መስዋዕቴን
ደጋግሜ ፡ አመልክሃለሁ ፡ ይህም ፡ ያንስሀል
ያለምንም ፡ ዋጋ ፡ እንዲሁ ፡ አድነኽኛል
(፪x)
ልቀኝልህ ፡ ልቀኝልህ
ላክብርህ ፡ ላክብርህ (፪x)

አዝበአዲስ ፡ በአዲስ ፡ ቅኔ ፡ እቀኝልሀለሁ ፡ እኔ
በአዲስ ፡ በአዲስ ፡ ዜማ ፡ ድምጼ ፡ ለአንተ ፡ ይሰማ
(፪x)
ከልቤ ፡ በሙሉ ፡ ሀይሌ (፪x)
አመሰግንሀለሁ ፡ ክብርን ፡ ለአንተ ፡ እሰጣለሁ (፪x)
ኢየሱስ (፪x)
ኢየሱስ (፬x)