From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አበቃ ፡ አከተመ ፡ አይሆንም ፡ በተባለበት
የጌታ ፡ ስም ፡ ሲጠራ ፡ ሁሉ ፡ ይዘራል ፡ ህይወት
ያለአንዳች ፡ እርዳታ ፡ ብቻውን ፡ ድንቅን ፡ አድርጐ
ልጆቹን ፡ ያሣርፋል ፡ በሀይሉ ፡ ተገለጦ
ታላቅነቱ ፡ አይወሰን ፡ ከ ፡ እስከ ፡ አይባልም
ብቻ ፡ እርሱ ፡ ይስራ ፡ እንጂ ፡ ማንም ፡ ፊቱ ፡ አይቆምም (፪x)
አዝ፦ ጌታችን ፡ ክንደብርቱ ፡ ነው (፫x)
የለም ፡ ሚገዳደረው ፡ አርሱ ፡ ብርቱ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ አሸናፊ ፡ ነው (፫x)
ማነው ፡ የሚቋቋመው ፡ አሸናፊ ፡ ነው (፪x)
ጽኑ ፡ ግንብ ፡ በጠላት ፡ ፊት ፡ የማይደፈር ፡ መከታ
ከክፋት ፡ ከሰይጣን ፡ እጅ ፡ የሚከልል ፡ ጌታ
ነው ፡ እኛ ፡ ምናመልከው ፡ ሀይለኛና ፡ ባለስልጣን
ተጠግተነው ፡ አርፈናል ፡ መደገፊያ ፡ ሆኖልን
ጥበቃው ፡ እጅግ ፡ ያስደንቃል ፡ ልጆቹን ፡ ያሳርፋል
ሀይሉም ፡ ከቶ ፡ አይደክምም ፡ በሰልፍ ፡ ይበረታል (፪x)
አዝ፦ ጌታችን ፡ ክንደብርቱ ፡ ነው (፫x)
የለም ፡ ሚገዳደረው ፡ አርሱ ፡ ብርቱ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ አሸናፊ ፡ ነው (፫x)
ማነው ፡ የሚቋቋመው ፡ አሸናፊ ፡ ነው (፪x)
ጌታ ፡ ከርሱ ፡ ጋር ፡ የሆነ ፡ ኽረ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ ያሻዋል
ከክንፎቹ ፡ በታች ፡ ሆኖ ፡ ተማምኖ ፡ ይኖራል
በክፉ ፡ ቀን ፡ አይሰጋም ፡ አምላኩ ፡ ይታደገዋል
ከረግረግ ፡ ከጭቃ ፡ አውጥቶ ፡ በአለት ፡ ያቆመዋል
ዛሬም ፡ ይህ ፡ ጌታ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ ፡ ካለ ፡ ምንደነው ፡ የሚያስፈራን
በእርሱ ፡ እየተማመንን ፡ በድል ፡ እንሄዳለን (፪x)
አዝ፦ ጌታችን ፡ ክንደብርቱ ፡ ነው (፫x)
የለም ፡ ሚገዳደረው ፡ አርሱ ፡ ብርቱ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ አሸናፊ ፡ ነው (፫x)
ማነው ፡ የሚቋቋመው ፡ አሸናፊ ፡ ነው (፪x)
ከጌታ ፡ የተነሳ ፡ በህይወት ፡ መኖር ፡ ችለናል
ካስጨናቂዎቻችን ፡ ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ አርፈናል
ማዳኑን ፡ የክንዱን ፡ ብርታት ፡ ባይናችን ፡ አሣይቶናል
ስለዚህም ፡ ልናከብረው ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ መጥተናል
ለክበሩ ፡ እንዘምራለን ፡ እናመሰግነዋለን
ጌታ ፡ ስለሚገባው ፡ እናመልከዋለን (፪x)
ምስጋና ፡ ለርሱ ፡ ይገባዋል (፫x)
ሌላ ፡ ምን ፡ ይሰጠዋል ፡ ለርሱ ፡ ይገባዋል (፬x)
|