ክበር (Keber) - ኃይለኢየሱስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኃይለኢየሱስ ፡ ታደሰ
(Haileyesuse Taddesse)

Haileyesuse Taddesse 1.jpg


(1)

አየሁ
(Ayehu)

ዓ.ም. (Year): ፳፻፮ (2013)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኃይለኢየሱስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Haileyesuse Taddesse)

 
እራሴን ፡ በራሴ ፡ እንዳላስገኘሁኝ
በአንተ ፡ እንደተሰራሁ ፡ ለአንተም ፡ እንደሆንኩኝ
ይገባኛል ፡ እና ፡ እዘዝ ፡ በህይወቴ
ከልካይ ፡ የለብህም ፡ የአንተ ፡ ነው ፡ እኔነቴ
 
አዝክበር (፫x) ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ንገስ (፫x) ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ክበር (፫x) ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ንገስ</u፡ > (፫x) ፡ የእኔ ፡ ጌታ

የምቆጥበው ፡ የምሰስተው
ክብር ፡ የለኝም ፡ ሁሉ ፡ የአንተ ፡ ነው (፪x)

ክበር (፫x) ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ንገስ</u፡ > (፫x) ፡ የእኔ ፡ ጌታ

ከአንተ ፡ ወዲህ ፡ ገዢ ፡ ከአንተ ፡ ሌላ ፡ አባት
ማን ፡ ሊነግስ ፡ ይወዳል ፡ ነፍሴንስ ፡ ሊሞላት
እኔ ፡ እንደው ፡ የአንተ ፡ ነኝ ፡ በደም ፡ የገዛኽኝ
የፍቅርህ ፡ ምቾቱ ፡ ሌላም ፡ አያሰኘኝ
 
አዝክበር (፫x) ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ንገስ (፫x) ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ክበር (፫x) ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ንገስ (፫x) ፡ የእኔ ፡ ጌታ

ክብር ፡ የማይገባኝ ፡ ያኔ ፡ ሳለው ፡ ከንቱ
ማነው ፡ የከፈለልኝ ፡ እዳዬን ፡ በሞቱ
ኢየሱስ ፡ አይደለህ ፡ ወይ ፡ ወርደህ ፡ ያነሳኽኝ
ታዲያ ፡ ክብሬ ፡ የቱ ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ለአንተ ፡ አልኩኝ

አዝክበር (፫x) ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ንገስ (፫x) ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ክበር (፫x) ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ንገስ (፫x) ፡ የእኔ ፡ ጌታ

በምስጋና ፡ ቅኔ ፡ ውዳሴ ፡ በመዝሙር
እጨምራለሁኝ ፡ ይሁን ፡ ለአንተ ፡ ክብር
ምኞቴ ፡ የስምህ ፡ ክብር ፡ መታሰቢያህም ፡ ነው
በቀንም ፡ በሌትም ፡ ናፍቆቴ ፡ ይሄ ፡ ነው

አዝክበር (፫x) ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ንገስ (፫x) ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ክበር (፫x) ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ንገስ (፫x) ፡ የእኔ ፡ ጌታ

የምቆጥበው ፡ የምሰስተው
ክብር ፡ የለኝም ፡ ሁሉ ፡ የአንተ ፡ ነው (፪x)

ክበር (፫x) ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ንገስ (፫x) ፡ የእኔ ፡ ጌታ

በምን ፡ ዓይነት ፡ ዜማ ፡ በምን ፡ ዓይነት
በብዙ ፡ ዓይነት ፡ ዜማ ፡ በብዙ ፡ ዓይነት
በምን ፡ ዓይነት ፡ ግጥም ፡ በምን ፡ ዓይነት
በብዙ ፡ ዓይነት ፡ ግጥም ፡ በብዙ ፡ ዓይነት (፪x)

ባመሰግንህ ፡ ይበቃል ፡ አልልም
እንዲያንስህ ፡ አውቃለው ፡ ይህ ፡ ለአንተ ፡ ትንሽ ፡ ነው (፬x)

ይህ ፡ ለአንተ ፡ ትንሽ ፡ ነው (፲x)