ሃሌሉያ (Hallelujah) - ኃይለኢየሱስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኃይለኢየሱስ ፡ ታደሰ
(Haileyesuse Taddesse)

Haileyesuse Taddesse 1.jpg


(1)

አየሁ
(Ayehu)

ዓ.ም. (Year): ፳፻፮ (2013)
ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኃይለኢየሱስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Haileyesuse Taddesse)

 
ማስተዋልህ ፡ በሊቅ ፡ አትመረመርም
እግዚአብሄር ፡ ታላቅ ፡ ነህ ፡ ማንም ፡ አላየህም
በላይ ፡ በከፍታ ፡ በክብር ፡ ትኖራለህ
በበረከትህም ፡ ምድርን ፡ ታጠግባለህ
ባለጠግነትህ ፡ አይጐድልም
ይፈቃል ፡ ይፈሳል ፡ ዘላለም (፪x)

አዝ፦ ሃሌሉያ ፡ ክብር ፡ ይገባሀልና
አምሣያ ፡ የሌለህ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ነህና (፪x)

የፊትህ ፡ ብርህን ፡ ከፀሐይ ፡ ይደምቃል
ሰባቱን ፡ ከዋክብት ፡ በእጆችህ ፡ ይዘሀል
አይኖችህ ፡ እንደ ፡ እሣት ፡ ነበልባሎች ፡ ናቸው
የራስህም ፡ ፀጉር ፡ ከነጭም ፡ ነጭ ፡ ነው
ማን ፡ መቆም ፡ ይችላል ፡ ካንተ ፡ ጋር
አይቶ ፡ ነፍስ ፡ ማን ፡ ይቀርለታል (፪x)

አዝ፦ ሃሌሉያ ፡ ክብር ፡ ይገባሀልና
አምሣያ ፡ የሌለህ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ነህና (፪x)

መላዕክት ፡ በፍርሀት ፡ ወድቀው ፡ ይሰግዱልሀል
ያምልኮአቸው ፡ ሽታ ፡ ቤትህን ፡ ሞልቶታል
ክብርና ፡ ውዳሴ ፡ ምስጋና ፡ ይገባሀል
እያሉ ፡ እራቱ ፡ እንስሶች ፡ ያከብሩሀል
ሽማግሌዎች ፡ ወድቀው ፡ የሰግዱልሀል
በፈቃድህ ፡ ሁሉን ፡ ፈጥረሀል
እያሉ ፡ ክብራቸውን ፡ ይሰጡሀል

አዝ፦ ሃሌሉያ ፡ ክብር ፡ ይገባሀልና
አምሣያ ፡ የሌለህ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ነህና (፪x)