በምህረትህ (Bemehereteh) - ኃይለኢየሱስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኃይለኢየሱስ ፡ ታደሰ
(Haileyesuse Taddesse)

Haileyesuse Taddesse 1.jpg


(1)

አየሁ
(Ayehu)

ዓ.ም. (Year): ፳፻፮ (2013)
ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኃይለኢየሱስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Haileyesuse Taddesse)

 
የሳተ ፡ ይመለስ ፡ የለም ፡ ወይ ፡ ከግድፈቱ
የወደቀስ ፡ ይጠገን ፡ የለም ፡ ወይ ፡ ከስብራቱ
አይኖቹን ፡ ሲያቀና ፡ በተስፋ ፡ ወደአንተ
ሲማፀን ፡ ምህረትን ፡ እየወተወተ
አይችልም ፡ መጨከን ፡ አንጀትህ ፡ የአባትነትህ
አጥበህ ፡ ታነፃለህ
አንተ ፡ ፍቅር ፡ ነህ
ይሄንን ፡ ላውራልህ

አዝ፦ ብደክም ፡ ወድቄ ፡ እንዳልቀር ፡ ፀጋህ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ያግዘኛል
ምህረትህ ፡ ከቁጣ ፡ ይፈጥናል ፡ እንድኖር ፡ ምክንያት ፡ ሆኖኛል
አልመካም ፡ መች ፡ ቆሜ ፡ ባቅሜ
ባትረዳኝ ፡ ሆነህ ፡ አጠገቤ ፡ ከጐኔ
(፪x)

በጨለማ ፡ ብቀመጥ ፡ ብርሀኔ ፡ ነህ
የሀጢያት ፡ ሸክም ፡ ቢያጐብጠኝም ፡ ታቀናኛለህ
ተስፋዬ ፡ ይቅርታ ፡ መጽናኛዬም ፡ ፊትህ ፡ ነው
ስለቸርነትህ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ምኖረው
ሲሰማኝ ፡ መኖርህ ፡ ሳስተውል ፡ መገኘትህን
መንፈሴ ፡ ያንስራራል
ነቅቶ ፡ ያዳምጥሀል
ጌታዬና ፡ አምላኬ ፡ ይልሃል

አዝ፦ ብደክም ፡ ወድቄ ፡ እንዳልቀር ፡ ፀጋህ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ያግዘኛል
ምህረትህ ፡ ከቁጣ ፡ ይፈጥናል ፡ እንድኖር ፡ ምክንያት ፡ ሆኖኛል
አልመካም ፡ መች ፡ ቆሜ ፡ ባቅሜ
ባትረዳኝ ፡ ሆነህ ፡ አጠገቤ ፡ ከጐኔ
(፪x)

ጉስቁልናዬን ፡ ስታይ ፡ አዘንክልኝ
እራርተህ ፡ እጅህን ፡ ዘረጋህ ፡ አቅፍህ ፡ ልታነሳኝ
ግድ ፡ የሚልህ ፡ ለኔ ፡ መጥፋቴን ፡ ማትወደው
ፊትህ ፡ ለኔ ፡ በራ ፡ በደሌንም ፡ ተውከው
እንደባሪያ ፡ መሆን ፡ ሳያንሰኝ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ ልጅ ፡ አልከኝ
እራሴን ፡ ልስጥህ ፡ ዝቅ ፡ ልበልልህ
ላንተው ፡ ኖሬ ፡ ላንተው ፡ ልሙትልህ

አዝ፦ ብደክም ፡ ወድቄ ፡ እንዳልቀር ፡ ፀጋህ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ያግዘኛል
ምህረትህ ፡ ከቁጣ ፡ ይፈጥናል ፡ እንድኖር ፡ ምክንያት ፡ ሆኖኛል
አልመካም ፡ መች ፡ ቆሜ ፡ ባቅሜ
ባትረዳኝ ፡ ሆነህ ፡ አጠገቤ ፡ ከጐኔ
(፪x)

በምህረትህ ፡ ብዛት ፡ ቤትህ ፡ እገባለሁ (፪x)
ስለምህረትህ ፡ ጌታ ፡ አመልክሃለሁ (፪x)

በፊትህ ፡ ሞገስ ፡ ያገኘሁት
አይደለም ፡ በእራሴ ፡ ያቆሙኩት
የፅድቅ ፡ የሥራ ፡ መልካም ፡ ነገር
ምህረትህ ፡ ድፍረት ፡ ሆኖልኝ ፡ ነው
የፀጋህ ፡ ማስቻሉ ፡ በዝቶልኝ ፡ ነው
ስምህን ፡ ላክብረው (፪x)