From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ አየሁ ፡ እኔስ ፡ እኔስ ፡ አየሁ
በዚህች ፡ እድሜ ፡ ስንቱን ፡ አየሁ
በዙፋኑ ፡ ፀንቶ ፡ ያለው
እግዚአብሔር ፡ ግን ፡ ሁሌም ፡ ያው ፡ ነው (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ግን ፡ ሁሌም ፡ ያው ፡ ነው (፮x)
ትላንት ፡ ሲታይ ፡ ማይደፈር ፡ ሲባል ፡ ዛሬ ፡ አይን ፡ ላፈር
አንቱ ፡ መባል ፡ ትላንት ፡ አንሶት ፡ ዛሬ ፡ አንተነት ፡ ሲበዛበት
ሰው ፡ ወዶ ፡ የሾመውን ፡ ሰው ፡ ወዶ ፡ ይሸረዋል (፪x)
ከእኛ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ ግን ፡ ማን ፡ ይስተካከላል
ከዘለአለምም ፡ እስከ ፡ ዘለአለም (፪x)
ነው ፡ መንግስቱ ፡ ጽኑ ፡ የሚመስለው ፡ የለም
አዝ፦ ህያው ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ህያው ፡ ነው (፪x)
ጌታ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x)
አንድ ፡ ሺ ፡ ቀን ፡ እንደአንድ ፡ ቀን
አንድ ፡ ቀንም ፡ አንደአንድ ፡ ሺ
ሁሌ ፡ ጌታ ፡ በዘመናት
ፈጣሪያቸው ፡ ለእለታት
በጊዜ ፡ አይገደብ ፡ እርሱ ፡ እግዚአብሐር ፡ ነው (፪x)
አመቶቹ ፡ አያልቁ ፡ ጸንቶ ፡ የሚኖር ፡ ነው
ያሳልፋል ፡ እንጂ ፡ እርሱ ፡ አንደው ፡ አያልፍም (፪x)
ተላንትናም ፡ ዛሬም ፡ ያው ፡ ነው ፡ ለዘላለም
አዝ፦ ህያው ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ህያው ፡ ነው (፪x)
ጌታ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x)
አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ እርሱ ፡ እኮ ፡ ነው
ለዘላለም ፡ ህያው ፡ እርሱ ፡ ነው
ላሞጋግሰው ፡ ይህን ፡ ጌታ
በጭብጨባ ፡ በእልልታ
ክብርና ፡ ሞገስም ፡ ባለጠግነትም ፡ ሊቀበል ፡ የሚገባው
ከጌቶቹ ፡ ጌታ ፡ ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ማን ፡ ነው
ግርማው ፡ የተለየ ፡ ባለ ፡ ብዙ ፡ ዝና (፪x)
ያለ ፡ አጋር ፡ እረዳት ፡ ብቻዉን ፡ ገናና
አዝ፦ ህያው ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ህያው ፡ ነው (፪x)
ጌታ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x)
ጌታ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x)
ህያው ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ህያው ፡ ነው (፪x)
ጌታ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x)
|