አምንሃለሁ (Amnehalehu) - ኃይለኢየሱስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኃይለኢየሱስ ፡ ታደሰ
(Haileyesuse Taddesse)

Haileyesuse Taddesse 1.jpg


(1)

አየሁ
(Ayehu)

ዓ.ም. (Year): ፳፻፮ (2013)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኃይለኢየሱስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Haileyesuse Taddesse)

 
አዝ፦ አምንሀለሁ ፡ ጌታ ፡ አምንሀለሁ
አምንሀለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ አምንሀለሁ (፪x)

ሠማይ ፡ ምድር ፡ ያልፍል ፡ ቃሌ ፡ ግን ፡ አያልፍም
ከአፌ ፡ የወጣዉ ፡ ቃል ፡ እንዲሁ ፡ አይመለስም
ብለህ ፡ እንደተናገርህ ፡ ቃልህን ፡ ፈጸምከዉ
ኮራሁብህ ፡ ኢየሱስ፡ አንተ ፡ በሰራኸዉ

ብታደርግ ፡ ልክ ፡ ብታፈርስ ፡ ልክ
የማትሣሣት ፡ ፍፁም ፡ የሆንክ
አንተ ፡ ሥራ ፡ እንጂ ፡ ቃልህን ፡ ላክና
ሚከለክልህ ፡ የቱ ፡ ነው ፡ ጀግና ፡ ከአንተ ፡ ወዲያ ፡ ጀግና

አዝ፦ አምንሀለሁ ፡ ጌታ ፡ አምንሀለሁ
አምንሀለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ አምንሀለሁ (፪x)

ሁኔታ ፡ ሚሰብከኝ ፡ ሚያስፈራ ፡ ነገር ፡ ነው
የሚታየው ፡ ሁሉ ፡ እጅግ ፡ አስደንጋጭ ፡ ነው
ቃልህ ፡ ትዝ ፡ ሲለኝ ፡ አይዞህ ፡ ነው ፡ የሚለኝ
እንዳልፈራ ፡ እንዳልዝል ፡ ነው ፡ የሚያስታውስኝ

መች ፡ በሰው ፡ ስሌት ፡ በአዋቂ ፡ መላ
ሆኖ ፡ ያውቅና ፡ የአንተ ፡ እኮ ፡ ሌላ
ዛሬ ፡ ርሃብ ፡ ሆኖ ፡ ነገ ፡ ጥጋብ ፡ ነው
ሥትል ፡ አምናለሁ ፡ ሁሉ ፡ የአንተ ፡ ነው
ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ነው

አዝ፦ አምንሀለሁ ፡ ጌታ ፡ አምንሀለሁ
አምንሀለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ አምንሀለሁ (፪x)

ውጣ ፡ ያልከኝ ፡ አንተ ፡ እንሆ ፡ ምድሪቷ
ሥሜን ፡ አውጅባት ፡ በርዝመት ፡ ስፋቱዋ
አብሬህ ፡ እሆናለሁ ፡ እስከ ፡ መጨረሻው
ሥትል ፡ ተቀበልኩኽ ፡ ካሳብህ ፡ ተስማማሁ

እንደ ፡ አባቶቼ ፡ በአንተ ፡ ታምኜ
እራሴን ፡ ክጄ ፡ በዓለም ፡ ጨክኜ
ከኖሩስ ፡ አይቀር ፡ እንዲህ ፡ ነው ፡ ኑሮ
አንተን ፡ አክብሮ ፡ ደሞ ፡ አስከብሮ (፪x)

ዛሬም ፡ ተመለክ ፡ አንተ ፡ አምላክ ፡ ነህ
ዛሬም ፡ ተደነቅ ፡ አንተ ፡ ድንቅ ፡ ንህ
ዛሬም ፡ ተወደስ ፡ አንተ ፡ ጀግና ፡ ነህ
ዛሬም ፡ ተሞገስ ፡ አንተ ፡ ልዩ ፡ ነህ

ሲያንሥህ ፡ ነው ፡ ጭብጨባ (፬x)
ሲያንሥህ ፡ ነው ፡ ዕልልታ (፬x)