አምልኮ ፡ አለኝ (Amleko Alegn) - ሐብታሙ ፡ ኩመላ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሐብታሙ ፡ ኩመላ
(Habtamu Kumela)

Habtamu Kumela 1.jpg


(1)

አጠገቤ ፡ ሆኗል
(Ategebie Honual)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሐብታሙ ፡ ኩመላ ፡ አልበሞች
(Albums by Habtamu Kumela)

አዝ፦ ተስፋ ፡ የሌለውን ፡ ሰው ፡ ተስፈኛ ፡ ላደረከው
ክብር ፡ ላላወቀውም ፡ ክብር ፡ ላሳየከው (፪x)
አምልኮ ፡ አለኝ ፡ አምልኮ (፪x)
ዝማሬ ፡ አለኝ ፡ ዝማሬ (፪x)

አምልኮ ፡ አለኝ ፡ ዝማሬ ፡ አለኝ
ክብር ፡ አለኝ ፡ ስግደት ፡ አለኝ (፪x)
አምልኮ ፡ አለኝ ፡ አምልኮ (፪x)
ዝማሬ ፡ አለኝ ፡ ዝማሬ (፪x)

ግራ ፡ ቀኙ ፡ ሁሉ ፡ ተስፋ ፡ ሚያስቆርጥ ፡ ነው
የሚሰማው ፡ ነገር ፡ አንገት ፡ ሚያስደፋ ፡ ነው
ግን ፡ የጌታዬን ፡ ድምጽ ፡ ቀና ፡ ስል ፡ ስሰማ
ተስፋ ፡ አለህ ፡ አለኝ ፡ ጠላቴ ፡ እየሰማ

ተስፋዬ ፡ ጌታዬ ፡ እኮ ፡ ነው
በዝማሬ ፡ እስቲ ፡ ላክብረው (፪x)

ተስፋዬ ፡ ጌታዬ ፡ እኮ ፡ ነው
በሽብሸባ ፡ እስቲ ፡ ላክብረው (፪x)

አዝ፦ ተስፋ ፡ የሌለውን ፡ ሰው ፡ ተስፈኛ ፡ ላደረከው
ክብር ፡ ላላወቀውም ፡ ክብር ፡ ላሳየከው (፪x)
አምልኮ ፡ አለኝ ፡ አምልኮ (፪x)
ዝማሬ ፡ አለኝ ፡ ዝማሬ (፪x)

ሁሉም ፡ በየፊናው ፡ በምርጫው ፡ ቢጓዝም
ከግብጽ ፡ ያወጣውን ፡ አምላኩን ፡ ባይመርጥም
በዘመን ፡ ፍጻሜ ፡ ከጌታ ፡ ሆነናል
በእኔና ፡ በእኔ ፡ ቤት ፡ ጌታ ፡ ይመለካል

አዝ፦ አምልኮ ፡ አለኝ ፡ ዝማሬ ፡ አለኝ
ክብር ፡ አለኝ ፡ ስግደት ፡ አለኝ (፪x)
አምልኮ ፡ አለኝ ፡ አምልኮ (፪x)
ዝማሬ ፡ አለኝ ፡ ዝማሬ (፪x)