የማይወጣ (Yemayeweta) - ጉለሌ ፡ ቤቴል ፡ ቤ/ክ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጉለሌ ፡ ቤቴል ፡ ቤ/ክ ፡ መዘምራን
(Gulelie Bethel Church Choir)

Lyrics.jpg


()

ሰላም ፡ አለ ፡ በኢየሱስ
(Selam Ale Beyesus)

ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 4:19
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጉለሌ ፡ ቤቴል ፡ ቤ/ክ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Gulelie Bethel Church Choir)

አዝ፦ የማይወጣ ፡ አቀበት ፡ የማይናድ ፡ ተራራ
የማይወረድ ፡ ቁልቁለት ፡ ለኢየሱስ ፡ የለምና
ጌታዬ ፡ ሁሉንም ፡ ሁሉንም ፡ የሚችል ፡ ነውና
ኢየሱስ ፡ ሁሉንም ፡ ሁሉንም ፡ የሚያስችል ፡ ነውና

የማይቻለው ፡ ለኢየሱስ ፡ ተችሎ
ሳየው ፡ ሳስተውለው ፡ ነገር ፡ ሁሉ ፡ አልፎ
አገኘዋለሁ ፡ ተቃንቶና ፡ አምሮ
ያቃተኝ ፡ ለእኔ ፡ ለጌታ ፡ ትንሽ ፡ ሆኖ

አዝ፦ የማይወጣ ፡ አቀበት ፡ የማይናድ ፡ ተራራ
የማይወረድ ፡ ቁልቁለት ፡ ለኢየሱስ ፡ የለምና
ጌታዬ ፡ ሁሉንም ፡ ሁሉንም ፡ የሚችል ፡ ነውና
ኢየሱስ ፡ ሁሉንም ፡ ሁሉንም ፡ የሚያስችል ፡ ነውና

ውጥንቅጡ ፡ ፊት ፡ ለፊት ፡ ተክቦ
የማይታለፍ ፡ ዳገት ፡ አቀበት ፡ ሆኖ
ያገደኝን ፡ አፈረሰ ፡ ንዶ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ድካሜን ፡ ተረድቶ

አዝ፦ የማይወጣ ፡ አቀበት ፡ የማይናድ ፡ ተራራ
የማይወረድ ፡ ቁልቁለት ፡ ለኢየሱስ ፡ የለምና
ጌታዬ ፡ ሁሉንም ፡ ሁሉንም ፡ የሚችል ፡ ነውና
ኢየሱስ ፡ ሁሉንም ፡ ሁሉንም ፡ የሚያስችል ፡ ነውና

ማዕበሉን ፡ ጐርፉን ፡ ስመለከት
በሀሳብ ፡ ስዋዥቅ ፡ ስንከራተት
ተራመድኩኝ ፡ መላዕክቱን ፡ አዘዘ
ድል ፡ ተደርጐ ፡ ጠላቴ ፡ ፈዘዘ

አዝ፦ የማይወጣ ፡ አቀበት ፡ የማይናድ ፡ ተራራ
የማይወረድ ፡ ቁልቁለት ፡ ለኢየሱስ ፡ የለምና
ጌታዬ ፡ ሁሉንም ፡ ሁሉንም ፡ የሚችል ፡ ነውና
ኢየሱስ ፡ ሁሉንም ፡ ሁሉንም ፡ የሚያስችል ፡ ነውና