ሰላም ፡ አለ ፡ በኢየሱስ (Selam Ale Beyesus) - ጉለሌ ፡ ቤቴል ፡ ቤ/ክ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጉለሌ ፡ ቤቴል ፡ ቤ/ክ ፡ መዘምራን
(Gulelie Bethel Church Choir)

Lyrics.jpg


()

ሰላም ፡ አለ ፡ በኢየሱስ
(Selam Ale Beyesus)

ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 6:00
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጉለሌ ፡ ቤቴል ፡ ቤ/ክ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Gulelie Bethel Church Choir)

አዝሰላም (፪x) ፡ አለ ፡ በኢየሱስ
እረፍት (፪x) ፡ አለ ፡ በኢየሱስ
ያልቀመስከው ፡ ክብር ፡ ዝና ፡ እየው (፪x)

የመዳን ፡ ቀን ፡ ዛሬ ፡ ነው ፡ አይለፍብህ
ጌታህን ፡ ተገናኝ ፡ ለፍርድ ፡ ሳይመጣብህ
በማሾፍ ፡ ከምታሳልፍ ፡ ወርቃማውን ፡ ጊዜህ
ቅመሰው ፡ ኢየሱስን ፡ ወንድሜ ፡ እባክህ

አዝሰላም (፪x) ፡ አለ ፡ በኢየሱስ
እረፍት (፪x) ፡ አለ ፡ በኢየሱስ
ያልቀመስከው ፡ ክብር ፡ ዝና ፡ እየው

በእጅህ ፡ ለመዳሰስ ፡ ሳትፈልግ ፡ ሳታምፅ
በእምነት ፡ ቅረብ ፡ ወደሱ ፡ አውርድ ፡ ሸክምህን
የፍርድ ፡ አምላክ ፡ መሆኑን ፡ ወንድሜ ፡ አትዘንጋ
ለሰው ፡ ልጅ ፡ ሁሉ ፡ ሲል ፡ ሕይወቱን ፡ የሰዋ

አዝሰላም (፪x) ፡ አለ ፡ በኢየሱስ
እረፍት (፪x) ፡ አለ ፡ በኢየሱስ
ያልቀመስከው ፡ ክብር ፡ ዝና ፡ እየው

ሰላምን ፡ ለማግኘት ፡ ከምድር ፡ መች ፡ ሆነ
ሰላም ፡ የሆነ ፡ ኢየሱስ ፡ በውስጥ ፡ ካልሰመነ
ደስታ ፡ ለማግኘት ፡ ብዙ ፡ አትባክን
በሞኝነት ፡ መጥተህ ፡ ኢየሱስን ፡ እመን

አዝሰላም (፪x) ፡ አለ ፡ በኢየሱስ
እረፍት (፪x) ፡ አለ ፡ በኢየሱስ
ያልቀመስከው ፡ ክብር ፡ ዝና ፡ እየው

ደስታን ፡ በዘፈን ፡ ሁሉን ፡ ሞክረሃል
እርካታን ፡ ለማግኘት ፡ ብዙ ፡ ተሯሩጠሃል
የመዳን ፡ ቀን ፡ ሳያልፍ ፡ ቀኑ ፡ ሳይጨልም
ሰላምን ፡ ለማግኘት ፡ በኢየሱስ ፡ መታመን

አዝሰላም (፪x) ፡ አለ ፡ በኢየሱስ
እረፍት (፪x) ፡ አለ ፡ በኢየሱስ
ያልቀመስከው ፡ ክብር ፡ ዝና ፡ እየው (፪x)