ምሥጋና ፡ ለአዳኛችን (Mesgana Ladagnachen) - ጉለሌ ፡ ቤቴል ፡ ቤ/ክ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጉለሌ ፡ ቤቴል ፡ ቤ/ክ ፡ መዘምራን
(Gulelie Bethel Church Choir)

Lyrics.jpg


()

ሰላም ፡ አለ ፡ በኢየሱስ
(Selam Ale Beyesus)

ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 4:20
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጉለሌ ፡ ቤቴል ፡ ቤ/ክ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Gulelie Bethel Church Choir)

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ለአዳኛችን ፡ ምሥጋና
ምሥጋና ፡ ለተቤዥን ፡ ምሥጋና
ምሥጋና ፡ ዛሬም ፡ ነገም ፡ ገናና
ለሆነው ፡ ኢየሱስ ፡ ነውና (፪x)

ጌታችንን ፡ እናክብር ፡ በአንድነት
ለሠራው ፡ ድንቅ ፡ ኑ ፡ እንስገድለት
እናመስግን ፡ በአፋችን ፡ ዝማሬ
የምሥጋና ፡ የድል ፡ ቀን ፡ ነው ፡ ዛሬ

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ለአዳኛችን ፡ ምሥጋና
ምሥጋና ፡ ለተቤዥን ፡ ምሥጋና
ምሥጋና ፡ ዛሬም ፡ ነገም ፡ ገናና
ለሆነው ፡ ኢየሱስ ፡ ነውና (፪x)

በአዲስ ፡ ቅኔ ፡ አመስግኑት ፡ ጌታን
እጅግ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ችሎታው
ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ክብሩ ፡ ሁሉ ፡ ገነነ
ጠላታችን ፡ ሥራው ፡ ተዳፈነ

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ለአዳኛችን ፡ ምሥጋና
ምሥጋና ፡ ለተቤዥን ፡ ምሥጋና
ምሥጋና ፡ ዛሬም ፡ ነገም ፡ ገናና
ለሆነው ፡ ኢየሱስ ፡ ነውና (፪x)

ጌታ ፡ ይክበር ፡ መታው ፡ ጠላታችን
በኢየሱስ ፡ ወድቋል ፡ ከሥራችን
በምሥጋና ፡ የከበረ ፡ ዜማ
በሰማይ ፡ ሰማያት ፡ ይሰማ

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ለአዳኛችን ፡ ምሥጋና
ምሥጋና ፡ ለተቤዥን ፡ ምሥጋና
ምሥጋና ፡ ዛሬም ፡ ነገም ፡ ገናና
ለሆነው ፡ ኢየሱስ ፡ ነውና (፪x)

የዘለዓለም ፡ ባለውለታ ፡ ነው
ከሰይጣን ፡ ኃይል ፡ ያዳነኝ ፡ ጀግና ፡ ነው
በዕልልታ ፡ እንዘምር ፡ በደስታ
አለኝታችን ፡ ክብራችን ፡ ነው ፡ ጌታ

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ለአዳኛችን ፡ ምሥጋና
ምሥጋና ፡ ለተቤዥን ፡ ምሥጋና
ምሥጋና ፡ ዛሬም ፡ ነገም ፡ ገናና
ለሆነው ፡ ኢየሱስ ፡ ነውና (፪x)