ጌታ ፡ ሆይ (Gieta Hoy) - ጉለሌ ፡ ቤቴል ፡ ቤ/ክ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጉለሌ ፡ ቤቴል ፡ ቤ/ክ ፡ መዘምራን
(Gulelie Bethel Church Choir)

Lyrics.jpg


()

ሰላም ፡ አለ ፡ በኢየሱስ
(Selam Ale Beyesus)

ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 4:21
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጉለሌ ፡ ቤቴል ፡ ቤ/ክ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Gulelie Bethel Church Choir)

ጌታ ፡ ሆይ ፡ ክንድህን ፡ ስናይ ፡ ብርታትህን ፡ ስናይ
ድል ፡ እናገኛለን ፡ በጠላታችን ፡ ላይ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህን ፡ ስናይ ፡ ክብርህን ፡ ስናይ
ልባችን ፡ ይሞላል ፡ በደስታ ፡ ከላይ

ጌታ ፡ ሆይ ፡ ፈውስህን ፡ ስናይ ፡ ማዳንህን ፡ ስናይ
እምነት ፡ ይሞላናል ፡ በጉዞአችን ፡ ላይ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ክብርህን ፡ ስናይ ፡ ግርማህን ፡ ስናይ
ፍርሃት ፡ ይሞላናል ፡ የመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ኃይል

ጌታ ፡ ሆይ ፡ ገድልህን ፡ ስናይ ፡ ሥራህን ፡ ስናይ
እናደንቅሃለን ፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ኃይል
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ግርማህ ፡ ሲያበራ ፡ ሥራህ ፡ ሲጐላ
ነፍሳችን ፡ በሀሴት ፡ በደስታ ፡ ተሞላ

ጌታ ፡ ሆይ ፡ ቃልህ ፡ ሲባርከን ፡ ፀጋህ ፡ ሲያቆመን
ተመሥገን ፡ ለማለት ፡ ታላቅ ፡ ኃይል ፡ አገኘን (፪x)