እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማነው (Ende Egziabhier Yale Manew) - ጉለሌ ፡ ቤቴል ፡ ቤ/ክ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጉለሌ ፡ ቤቴል ፡ ቤ/ክ ፡ መዘምራን
(Gulelie Bethel Church Choir)

Lyrics.jpg


()

ሰላም ፡ አለ ፡ በኢየሱስ
(Selam Ale Beyesus)

ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 6:05
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጉለሌ ፡ ቤቴል ፡ ቤ/ክ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Gulelie Bethel Church Choir)

አዝ፦ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማነው
ተስፋ ፡ በሌለበት ፡ ጭልምልም ፡ ባለበት
ስሜትን ፡ አዋቂ ፡ በልብም ፡ ዘላቂ (፪x)

የጠላቴ ፡ ሰልፍ ፡ በርትቶብኝ
ስፍራዬን ፡ እስክለቅ ፡ አስጨንቆኝ
በክንፎቹ ፡ ጥላ ፡ ጋረደኝ
ጋሻ ፡ ረድኤቴ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆነልኝ

አዝ፦ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማነው
ተስፋ ፡ በሌለበት ፡ ጭልምልም ፡ ባለበት
ስሜትን ፡ አዋቂ ፡ በልብም ፡ ዘላቂ (፪x)

በጨካኞች ፡ ቁጣ ፡ አስትንፋስ
ህዝብህን ፡ በሚመታ ፡ አውሎ ፡ ነፍስ
በችግሬ ፡ በጭንቄ ፡ ሰዓት
መመኪያዬ ፡ እፎይ ፡ ያልኩበት

አዝ፦ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማነው
ተስፋ ፡ በሌለበት ፡ ጭልምልም ፡ ባለበት
ስሜትን ፡ አዋቂ ፡ በልብም ፡ ዘላቂ (፪x)

ሀዘን ፡ ጭንቀት ፡ እጅግ ፡ በዝቶብኝ
መራመድ ፡ አቅቶኝ ፡ ጨልሞብኝ
እግዚአብሔር ፡ ሆነ ፡ ብርሃኔ
ላመስግነው ፡ በአዲስ ፡ ቅኔ

አዝ፦ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማነው
ተስፋ ፡ በሌለበት ፡ ጭልምልም ፡ ባለበት
ስሜትን ፡ አዋቂ ፡ በልብም ፡ ዘላቂ (፪x)

የልቤ ፡ አምላክ ፡ እርሱ ፡ ታላቅ ፡ ነው
በማግኘት ፡ በማጣቴ ፡ የማመልከው
ሆኖልኛል ፡ ለፀሎቴ ፡ መልስ
አክብረዋለሁ ፡ በእኔ ፡ እንዲነግሥ

አዝ፦ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማነው
ተስፋ ፡ በሌለበት ፡ ጭልምልም ፡ ባለበት
ስሜትን ፡ አዋቂ ፡ በልብም ፡ ዘላቂ (፪x)

ምሥጋናው ፡ ምድርን ፡ የሞላ
የፍጥረታት ፡ ገዢ ፡ የለም ፡ ሌላ
በጥበቡ ፡ አቻ ፡ የሌለው
አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ አምላካችን ፡ ነው

አዝ፦ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማነው
ተስፋ ፡ በሌለበት ፡ ጭልምልም ፡ ባለበት
ስሜትን ፡ አዋቂ ፡ በልብም ፡ ዘላቂ (፪x)