እግዚአብሔር ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ነው (Egziabhier Bezufanu Lay New) - ጉለሌ ፡ ቤቴል ፡ ቤ/ክ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጉለሌ ፡ ቤቴል ፡ ቤ/ክ ፡ መዘምራን
(Gulelie Bethel Church Choir)

Lyrics.jpg


()

ሰላም ፡ አለ ፡ በኢየሱስ
(Selam Ale Beyesus)

ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 4:41
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጉለሌ ፡ ቤቴል ፡ ቤ/ክ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Gulelie Bethel Church Choir)

አዝእግዚአብሔር ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ነው (፫x)
ማን ፡ ነው ፡ የሚረታው (፪x)

ብዙዎች ፡ ተነሱ ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ ሊገጥሙ
መች ፡ ተሳካላቸው ፡ ተንኮታኩተው ፡ ቀሩ
ዛሬም ፡ በዙፋኑ ፡ ተንሰራፍቶ ፡ ይኖራል
ኃይለኛው ፡ እግዚአብሔርን ፡ ማንስ ፡ ይረታዋል ?

አዝእግዚአብሔር ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ነው (፫x)
ማን ፡ ነው ፡ የሚረታው (፪x)

ጐልያድን ፡ በድፍረት ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ ተነስቶ
ተገዳድሮት ፡ ነበር ፡ ጡንቻውን ፡ ተማምኖ [1]
በዙፋኑ ፡ ያለው ፡ እግዚአብሔር ፡ ጌታ ፡ ነው
ተዘርሮ ፡ ቀረ ፡ ጌታዬ ፡ አሸነፈው [2]

አዝእግዚአብሔር ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ነው (፫x)
ማን ፡ ነው ፡ የሚረታው (፪x)

ዕቅዱን ፡ እንዳይፈፅም ፡ ማነው ፡ የሚያግደው
ድንቅን ፡ እንዳይሰራ ፡ ማንስ ፡ ተቋቋመው
ሁሉን ፡ የሚረታ ፡ የነገሥታት ፡ ንጉሥ ፡ ነው
ዛሬም ፡ በዚህ ፡ ዘመን ፡ ጌታችን ፡ ጌታ ፡ ነው

አዝእግዚአብሔር ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ነው (፫x)
ማን ፡ ነው ፡ የሚረታው (፪x)

  1. ፩ ሳሙኤል ፲፯ ፡ ፰ - ፲፩ (1 Samuel 17:8-11)
  2. ፩ ሳሙኤል ፲፯ ፡ ፴፪ - ፶፩ (1 Samuel 17:32-51)