ቸርነቱን ፡ ምህረቱን (Cherenetun Meheretun) - ጉለሌ ፡ ቤቴል ፡ ቤ/ክ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጉለሌ ፡ ቤቴል ፡ ቤ/ክ ፡ መዘምራን
(Gulelie Bethel Church Choir)

Lyrics.jpg


()

ሰላም ፡ አለ ፡ በኢየሱስ
(Selam Ale Beyesus)

ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 5:23
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጉለሌ ፡ ቤቴል ፡ ቤ/ክ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Gulelie Bethel Church Choir)

አዝ፦ ቸርነቱን ፡ ምህረቱን ፡ ከእኔ ፡ ላይ ፡ አላራቀም
የአብርሃም ፡ አምላክ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይባረክ (፪x)

ገደላ ፡ ገደሉን ፡ ሸለቆ ፡ ስምጥ ፡ ዋሻ ፡ አስፈሪው
በሰው ፡ የማይደፈረውን ፡ በአምላኬ ፡ አልፌው
ዓይኔን ፡ የማነሳበት ፡ አንዳች ፡ ተስፋ ፡ ሳይኖረኝ
ሰማሁ ፡ የጌታዬን ፡ ድምፅ ፡ አለሁ ፡ ሲለኝ ፡ ሊረዳኝ

አዝ፦ ቸርነቱን ፡ ምህረቱን ፡ ከእኔ ፡ ላይ ፡ አላራቀም
የአብርሃም ፡ አምላክ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይባረክ (፪x)

በምድር ፡ እንደ ፡ ተፈጠረ ፡ መልካም ፡ ፍሬ ፡ እንዲያፈራ
ሊያይ ፡ ሲናፍቅ ፡ ጌታ ፡ ፍሬው ፡ ሁሉ ፡ ሲጐመራ
በሕይወት ፡ መሆኔ ፡ ቀርቶ ፡ የሞት ፡ ሸታ ፡ ሆኜ ፡ አገኘኝ
ጌታዬ ፡ ግን ፡ በምህረቱ ፡ ዳግም ፡ ለክብሩ ፡ አቆመኝ

አዝ፦ ቸርነቱን ፡ ምህረቱን ፡ ከእኔ ፡ ላይ ፡ አላራቀም
የአብርሃም ፡ አምላክ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይባረክ (፪x)

የድልን ፡ ተስፋ ፡ አያለሁ ፡ ምህረት ፡ ከጌታ ፡ ዘንድ ፡ ነው
የከበበኝን ፡ ጠላት ፡ ዳግም ፡ በዓይኔ ፡ ላላየው
ምህረቱ ፡ ለእኔ ፡ በዝቶ ፡ ክብሩን ፡ ላወራ ፡ ችያለሁ
የቸርነቱ ፡ ተካፋይ ፡ ሆኜ ፡ እኔም ፡ ስላየሁ

አዝ፦ ቸርነቱን ፡ ምህረቱን ፡ ከእኔ ፡ ላይ ፡ አላራቀም
የአብርሃም ፡ አምላክ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይባረክ (፪x)