ብሩክ ፡ ይሁን (Beruk Yehun) - ጉለሌ ፡ ቤቴል ፡ ቤ/ክ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጉለሌ ፡ ቤቴል ፡ ቤ/ክ ፡ መዘምራን
(Gulelie Bethel Church Choir)

Lyrics.jpg


()

ሰላም ፡ አለ ፡ በኢየሱስ
(Selam Ale Beyesus)

ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 2:40
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጉለሌ ፡ ቤቴል ፡ ቤ/ክ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Gulelie Bethel Church Choir)

የዘለዓለም ፡ እግዚአብሔር ፡ የቅዱሳን ፡ መታመኛ
በትካዜ ፡ በመከራ ፡ መጠለያ ፡ ነው ፡ መፅናኛ
ቅዱስ ፡ አምላክ ፡ የዘላለም
የሚመስለው ፡ ፍፁም ፡ የለም (፪x)

አዝ፦ ብሩክ ፡ ይሁን ፡ የእግዚአብሔር ፡ ሥም
ብሩክ ፡ ይሁን ፡ አሜን (፪x)

ልምላሜም ፡ በረከት ፡ ከእርሱ ፡ በሚሆን ፡ ደስታ
አፍሶልናል ፡ እግዚአብሔር ፡ ዘለዓለማዊን ፡ እርካታ
ምርጫችን ፡ አምላካችን ፡ ነው
ያዋጣናል ፡ ብለን ፡ የያዝነው (፪x)

አዝ፦ ብሩክ ፡ ይሁን ፡ የእግዚአብሔር ፡ ሥም
ብሩክ ፡ ይሁን ፡ አሜን (፪x)

አደራን ፡ በመጠበቁ ፡ ፍፁም ፡ ሆኖ ፡ የታመነ
መንፈስ ፡ ነፍስና ፡ ሥጋ ፡ ያለ ፡ ነውር ፡ የጠበቀ
ከእኛ ፡ ጋር ፡ ሆኖ ፡ እስካሁን
ጠብቆናል ፡ በሕይወታችን (፪x)

አዝ፦ ብሩክ ፡ ይሁን ፡ የእግዚአብሔር ፡ ሥም
ብሩክ ፡ ይሁን ፡ አሜን (፪x)