አሜን ፡ ሁሉን ፡ ትችላለህ (Amien Hulun Techelaleh) - ጉለሌ ፡ ቤቴል ፡ ቤ/ክ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጉለሌ ፡ ቤቴል ፡ ቤ/ክ ፡ መዘምራን
(Gulelie Bethel Church Choir)

Lyrics.jpg


()

ሰላም ፡ አለ ፡ በኢየሱስ
(Selam Ale Beyesus)

ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:20
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጉለሌ ፡ ቤቴል ፡ ቤ/ክ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Gulelie Bethel Church Choir)

አዝ፦ አሜን ፡ ሁሉን ፡ ትችላለህ
አሜን ፡ ሁሉን ፡ ታደርጋለህ
የለም ፡ የሚያቅትህ (፪x)

በሰማይ ፡ በምድር ፡ ሥልጣን ፡ ነው ፡ በእጅህ
ከአቅምህ ፡ በላይ ፡ ሆኖ ፡ የለም ፡ የሚያቅትህ
ዕቅድ ፡ ስታደርግ ፡ ሀሳብህን ፡ ስትፈፅም
ከቶ ፡ ማን ፡ ይችላል ፡ ፈቃድህን ፡ ሊቋቋም

አዝ፦ አሜን ፡ ሁሉን ፡ ትችላለህ
አሜን ፡ ሁሉን ፡ ታደርጋለህ
የለም ፡ የሚያቅትህ (፪x)

ተስፋ ፡ ለቆረጠ ፡ ተስፋ ፡ ትሆናለህ
በሞተ ፡ ሕይወት ፡ ውስጥ ፡ ነፍስን ፡ ተዘራለህ
የቆሰለውንም ፡ ትፈውሰዋለህ
በምድር ፡ በሰማይ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ጌታ ፡ ነህ

አዝ፦ አሜን ፡ ሁሉን ፡ ትችላለህ
አሜን ፡ ሁሉን ፡ ታደርጋለህ
የለም ፡ የሚያቅትህ (፪x)

ብዙ ፡ ወጥተን ፡ ወርደን ፡ መልስ ፡ ላጣንለት
ተጨንቀን ፡ ተጠበን ፡ ለጐሰቆልንበት
ድምፅህን ፡ ስትልክ ፡ ታበጃጀዋለህ
ለችግሮቻችን ፡ መፍትሄው ፡ አንተ ፡ ነው

አዝ፦ አሜን ፡ ሁሉን ፡ ትችላለህ
አሜን ፡ ሁሉን ፡ ታደርጋለህ
የለም ፡ የሚያቅትህ (፪x)

በቅዱሳንህ ፡ ላይ ፡ አላማህ ፡ ፍቅር ፡ ነው
ሀሳብህ ፡ ጥልቅ ፡ ነው ፡ ማንም ፡ አይችል ፡ ሊያውቀው
በክፉ ፡ በመልካም ፡ ተስኬዳቸዋለህ
በቃልህ ፡ ማንሳትን ፡ ትችልበታለህ

አዝ፦ አሜን ፡ ሁሉን ፡ ትችላለህ
አሜን ፡ ሁሉን ፡ ታደርጋለህ
የለም ፡ የሚያቅትህ (፪x)