From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
በሰማያት ፡ ካለው ፡ ከክብር ፡ ዙፋኔ
ክብሬን ፡ ሁሉ ፡ ትቼ ፡ መውረዴ ፡ እኔ
አምላክ ፡ ሆኜ ፡ ሳለሁ ፡ ከበረት ፡ ማደሬ
ለአንተ ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ እንዲህ ፡ መዋረዴ
አዝ፦ ተው ፡ ተመለስ ፡ ልጄ ፡ ወደ ፡ ቀድሞው ፡ ስፍራህ
እባክህ ፡ አድምጠኝ ፡ ቆሜ ፡ ስጣራ
ዓይኔ ፡ እያየችህ ፡ ወደ ፡ ሞት ፡ ስትሄድ
አንጀቴ ፡ ታወከች ፡ ለእሳት ፡ ስትሟገት
ተው ፡ ተመለስ ፡ ልጄ ፡ ወደ ፡ ቀድሞው ፡ ስፍራህ
የጭንቄ ፡ ተካፋይ ፡ አጋዥም ፡ ሳይኖረኝ
የሞት ፡ ጣርም ፡ ይዞኝ ፡ የደም ፡ ላብ ፡ ሲያልበኝ
ይህን ፡ መከራዬን ፡ እንዴት ፡ እረሳኸው
ፊትህን ፡ አዙረህ ፡ እኔን ፡ የከዳኸው
አዝ፦ ተው ፡ ተመለስ ፡ ልጄ ፡ ወደ ፡ ቀድሞው ፡ ስፍራህ
እባክህ ፡ አድምጠኝ ፡ ቆሜ ፡ ስጣራ
ዓይኔ ፡ እያየችህ ፡ ወደ ፡ ሞት ፡ ስትሄድ
አንጀቴ ፡ ታወከች ፡ ለእሳት ፡ ስትሟገት
ተው ፡ ተመለስ ፡ ልጄ ፡ ወደ ፡ ቀድሞው ፡ ስፍራህ
በጅራፍ ፡ ስገረፍ ፡ ሥጋዬም ፡ ሲቆረስ
በጦር ፡ ተወግቼ ፡ ደሜ ፡ እንደውኃ ፡ ሲፈስ
የሾህ ፡ አክሊል ፡ ጭኜ ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ መሞቴ
እባክህ ፡ ይሰማህ ፡ ይህ ፡ ለማን ፡ ነው ፡ ልጄ
አዝ፦ ተው ፡ ተመለስ ፡ ልጄ ፡ ወደ ፡ ቀድሞው ፡ ስፍራህ
እባክህ ፡ አድምጠኝ ፡ ቆሜ ፡ ስጣራ
ዓይኔ ፡ እያየችህ ፡ ወደ ፡ ሞት ፡ ስትሄድ
አንጀቴ ፡ ታወከች ፡ ለእሳት ፡ ስትሟገት
|