From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ ምሥጋና ፡ ይሁን ፡ ምሥጋና
ምሥጋና ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና
ይዘመናቱ ፡ የታሪክ ፡ ጌታ
የእኛ ፡ ኢየሱስ ፡ የማይረታ (፪x)
ብዙ ፡ ብርቱዎች ፡ በምድር ፡ ነበሩ
ሊገዳደሩ ፡ ፍፁም ፡ የጣሩ
ስራቸው ፡ ሁሉ ፡ እንደጉም ፡ በኗል
አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ዛሬም ፡ ከብረሃል
አዝ፦ ምሥጋና ፡ ይሁን ፡ ምሥጋና
ምሥጋና ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና
ይዘመናቱ ፡ የታሪክ ፡ ጌታ
የእኛ ፡ ኢየሱስ ፡ የማይረታ (፪x)
በዘመናት ፡ ውስጥ ፡ የተቋቋመህ
ከቶ ፡ ማን ፡ ነበር ፡ አንተን ፡ የረታህ
ትጥቅህ ፡ ጠንካራ ፡ ብርቱ ፡ ሰልፈኛ
የእኛ ፡ ኢየሱስ ፡ ታላቅ ፡ ጦረኛ
አዝ፦ ምሥጋና ፡ ይሁን ፡ ምሥጋና
ምሥጋና ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና
ይዘመናቱ ፡ የታሪክ ፡ ጌታ
የእኛ ፡ ኢየሱስ ፡ የማይረታ (፪x)
በምድር ፡ በሰማይ ፡ ይህ ፡ ሥልጣን ፡ ያለህ
ፍጥረታት ፡ ሁሉ ፡ የሚሰግዱልህ
ሞገስህ ፡ ትልቅ ፡ ወሰን ፡ የሌለው
የእስራኤል ፡ ቅዱስ ፡ ሚመስልህ ፡ ማነው
አዝ፦ ምሥጋና ፡ ይሁን ፡ ምሥጋና
ምሥጋና ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና
ይዘመናቱ ፡ የታሪክ ፡ ጌታ
የእኛ ፡ ኢየሱስ ፡ የማይረታ (፪x)
|