መድኃኒቴ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነው (Medhanitie Bezu Bezu New) - ግሩም ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ግሩም ፡ ታደሰ
(Girum Tadesse)

Lyrics.jpg


(1)

መድኃኒቴ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነው
(Medhanitie Bezu Bezu New)

ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 4:36
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የግሩም ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Girum Tadesse)

መድሃኒቴ ብዙ ብዙ ነው ለኔ ያረገው ያረገው/2/
እንደገና ስሙን ላክብረው ውለታው ለኔ ብዙ ነው

መንገድ ላይ ወድቄ ጠላቴ አቁስሎኝ
ማንም አልነበረም ከውድቀት ያነሳኝ
ዘይቱን አፍስሶ ቁስሎቼን የቀባኝ
እንደ ኢየሱሴ የለኝም አዳኝ

ሰው ወዳጁን ሲወድ በጥቂቱ ነው
ጥቅሙ ሲቀር ፍቅሩም ቀሪ ነው
እኔ ግን ጠላትህ ሳለሁ ወደድከኝ
በዘላለም ፍቅርህ ኢየሱስ አሰብከኝ

ድካም ችግሬን የምትሸፍንልኝ
ምርኩዝ ድጋፌ ጋሻም የሆንከኝ
ከእናት ከአባቴም የምትበልጥብኝ
መድሃኒቴ ሆይ ከፍ በልልኝ

አንድ ሁለት ብዬ ቁጥር ብሰጠው
ጌታ ውለታው ከልክ በላይ ነው
እንደ እኔ ውለታው የበዛላችሁ
ቅኔን ተቀኙለት እልል ብላችሁ