From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ትቶኛል ፡ ለምን ፡ ትይኛለሽ
የመከራሽን ፡ ቀን ፡ ማነው ፡ ያሳለፈሽ
ለአንቺ ፡ የማላስብ ፡ ጨካኝ ፡ አይደለሁም
ዝም ፡ ብልሽ ፡ እንኳን ፡ ቢሆን ፡ አልረሳሽም
ለአንቼ ፡ የገባሁትን ፡ የተስፋ ፡ ቃሌን
ምነው ፡ በጥቂቱ ፡ ተጠራጠርሺኝ
በሃዘን ፡ አልቅሰሽ ፡ ለምን ፡ አስጨነቅሺኝ
ስለምንስ ፡ ልጄ ፡ ጌታ ፡ ረሳኝ ፡ አልሺኝ
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ትቶኛል ፡ ለምን ፡ ትይኛለሽ
የመከራሽን ፡ ቀን ፡ ማነው ፡ ያሳለፈሽ
ለአንቺ ፡ የማላስብ ፡ ጨካኝ ፡ አይደለሁም
ዝም ፡ ብልሽ ፡ እንኳን ፡ ቢሆን ፡ አልረሳሽም
የሚያጽናናኝ ፡ የለም ፡ መንገድ ፡ ዳር ፡ ጥሎኛል
እግዚአብሔር ፡ እንደሰው ፡ ፊቱን ፡ ከእኔ ፡ አዙሯል
ተለዋዋጭ ፡ አምላክ ፡ እንደሰው ፡ ሆነብኝ
ብለሽ ፡ አምተሽኛል ፡ ጌታዬ ፡ እንኳን ፡ ጣለኝ
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ትቶኛል ፡ ለምን ፡ ትይኛለሽ
የመከራሽን ፡ ቀን ፡ ማነው ፡ ያሳለፈሽ
ለአንቺ ፡ የማላስብ ፡ ጨካኝ ፡ አይደለሁም
ዝም ፡ ብልሽ ፡ እንኳን ፡ ቢሆን ፡ አልረሳሽም
በሃዘን ፡ ቀጠረኝ ፡ በድካም ፡ ከበበኝ
ፍርዴን ፡ አጣመመው ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ተወኝ
በሙላት ፡ ከቤቴ ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ መጣሁኝ
ባዶዬን ፡ አስቀረኝ ፡ ስለምንስ ፡ አልሽኝ
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ትቶኛል ፡ ለምን ፡ ትይኛለሽ
የመከራሽን ፡ ቀን ፡ ማነው ፡ ያሳለፈሽ
ለአንቺ ፡ የማላስብ ፡ ጨካኝ ፡ አይደለሁም
ዝም ፡ ብልሽ ፡ እንኳን ፡ ቢሆን ፡ አልረሳሽም
ጉድጓድ ፡ እንድትገቢ ፡ ጠላት ፡ ከማሰልሽ
ከእሳት ፡ አውጥቼሽ ፡ ከመቼው ፡ ተረሳሽ
እስቲ ፡ መለሽ ፡ ብለሽ ፡ ባርኮጽህን ፡ ቁተሪ
እባክሽን ፡ ልጄ ፡ እንዲህ ፡ አታምርሪ
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ትቶኛል ፡ ለምን ፡ ትይኛለሽ
የመከራሽን ፡ ቀን ፡ ማነው ፡ ያሳለፈሽ
ለአንቺ ፡ የማላስብ ፡ ጨካኝ ፡ አይደለሁም
ዝም ፡ ብልሽ ፡ እንኳን ፡ ቢሆን ፡ አልረሳሽም
አጭር ፡ ዝምታዬ ፡ ነው ፡ ወይ ፡ ያስመረረሽ
ጭር ፡ ያለው ፡ በረሃ ፡ ያጣልኩ ፡ ያስመሰለሽ
በክረምቱ ፡ ዝናብ ፡ እረሰርስሻለሁ
ያስጨነቀሽንም ፡ ሁሉ ፡ ገስጻለሁ
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ትቶኛል ፡ ለምን ፡ ትይኛለሽ
የመከራሽን ፡ ቀን ፡ ማነው ፡ ያሳለፈሽ
ለአንቺ ፡ የማላስብ ፡ ጨካኝ ፡ አይደለሁም
ዝም ፡ ብልሽ ፡ እንኳን ፡ ቢሆን ፡ አልረሳሽም
እስቲ ፡ አመስግኒኝ ፡ ማልቀሱን ፡ ተይና
ጠላትሽን ፡ በፊቴ ፡ አሳፍሪውና
በቤትሽ ፡ በጓዳሽ ፡ ሁሉ ፡ እገባና
አነቃሻለሁ ፡ ዳግም ፡ እሰራሽና
ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ ስላሰብከን
ተመስገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ስላየኸን
ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ ስላሰብከን
|