From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ በዘላለም ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ተቀምጠህ ፡ ያለህ
በሰማይም ፡ በምድርም ፡ ሙሉ ፡ ስልጣን ፡ ያለህ
ዙፋንህ ፡ ተነቃንቆ ፡ ተገርስሶ ፡ የት ፡ ያውቃል
እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ
ዘንዶውን ፡ ገጠመክ ፡ አሸነፍክ ፡ ጌታ
በኃይል ፡ በሰልፍም ፡ የምትበረታ
ፅኑ ሀያላንን ሁሉ ፡ ያሸነፍክ
የኃያል ፡ ኃያል ፡ ኢየሱስ ፡ ብርቱ ፡ ነህ
አዝ፦ በዘላለም ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ተቀምጠህ ፡ ያለህ
በሰማይም ፡ በምድርም ፡ ሙሉ ፡ ስልጣን ፡ ያለህ
ዙፋንህ ፡ ተነቃንቆ ፡ ተገርስሶ ፡ የት ፡ ያውቃል
እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ
ኃይልህ ፡ ከኃያላን ፡ ሁሉ ፡ ይበልጣል
ውሀን ፡ እንደ ፡ ግንብ ፡ ቀጥ ፡ አድርጎ ፡ ያቆማል
ከአጥፊዎችም ፡ እጅ ፡ ክንድህ ፡ ያስጥላል
የይሁዳ ፡ አንበሳ ፡ ማን ፡ ይመስልሀል
አዝ፦ በዘላለም ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ተቀምጠህ ፡ ያለህ
በሰማይም ፡ በምድርም ፡ ሙሉ ፡ ስልጣን ፡ ያለህ
ዙፋንህ ፡ ተነቃንቆ ፡ ተገርስሶ ፡ የት ፡ ያውቃል
እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ
ኃይልህን ፡ ሳያውቁ ፡ የተነሱብህ
አስከትተው ፡ ጦር ፡ የዘመቱብህ
ክንድህ ፡ ገጥሟቸው ፡ ተሸንፈዋል
ሥራቸው ፡ ጠፍቶ ፡ አንተ ፡ ነግሰሀል
አዝ፦ በዘላለም ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ተቀምጠህ ፡ ያለህ
በሰማይም ፡ በምድርም ፡ ሙሉ ፡ ስልጣን ፡ ያለህ
ዙፋንህ ፡ ተነቃንቆ ፡ ተገርስሶ ፡ የት ፡ ያውቃል
እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ
ሰማይ ፡ ምድርን ፡ በስልጣንህ ፡ ቃል
ፍጥረት ፡ አስኪደነቅ ፡ ሰርተሀቸዋል
ስላልተገኘልህ ፡ ከቶ ፡ ላንተ ፡ አቻ
ሥምህ ፡ ገነነ ፡ እስከ ፡ ምድር ፡ ዳርቻ
አዝ፦ በዘላለም ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ተቀምጠህ ፡ ያለህ
በሰማይም ፡ በምድርም ፡ ሙሉ ፡ ስልጣን ፡ ያለህ
ዙፋንህ ፡ ተነቃንቆ ፡ ተገርስሶ ፡ የት ፡ ያውቃል
እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ
|