የማልጠግበው (Yemaltegbew) - ግሩም ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ግሩም ፡ ታደሰ
(Girum Tadesse)

Girum Tadesse 3.jpg


(3)

ከልቤ ፡ የፈለቀ
(Kelebie Yefeleqe)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የግሩም ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Girum Tadesse)

 
ከሞት ፡ የበረታ ፡ ፍቅሩ ፡ አሽነፈኝ
ነፍስም ፡ አልቀረልኝ ፡ ወድጄዋለሁኝ
ሰዎች ፡ ሌላም ፡ ቢሉም ፡ ለእኔ ፡ ግን ፡ ፍቅር ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ብዬ ፡ የማልጠግበው

አዝ፦ የማልጠግበው ፡ እኔስ ፡ የማልጠግበው
የማልጠግበው ፡ እኔስ ፡ ኢየሱሴን ፡ ነው (፪x)

በመልካምነቱ ፡ ደስታን ፡ አጠገበኝ (፪x)
ባርኮቱ ፡ በሞላው ፡ ድንኳኑ ፡ ያኖረኝ (፪x)
ሥጋት ፡ ቀርቶልኛል ፡ ተደላድያለሁ (፪x)
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ነው ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ያለው (፪x)

አዝ፦ ከሰው ፡ ሁሉ ፡ ልዩ ፡ እርሱን ፡ የሚያደርገው
ፍቅሩ ፡ ወረት ፡ አያውቅ ፡ ዘለዓለማዊ ፡ ነው (፪x)

የሚከታተለኝ ፡ በሄድኩበት ፡ ቦታ (፪x)
ዐይኖቹ ፡ ዐይነሱም ፡ ከእኔ ፡ ላይ ፡ ለአንድ ፡ አፍታ (፪x)
የገባኝ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ እንዲሁ ፡ ወዶኛል (፪x)
ፍቅሩም ፡ ከማር ፡ ይልቅ ፡ እጅግ ፡ ይጣፍጣል (፪x)

አዝ፦ ከወይን ፡ ጠጅ ፡ ይልቅ ፡ ፍቅሩ ፡ አጥግቦኛል
እኔስ ፡ ሌላ ፡ አልሻም ፡ ኢየሱስ ፡ ይበቃኛል (፪x)

ያስደንቀኝ ፡ ጀመረ ፡ እየዋለ ፡ እያደር (፪x)
በእኔ ፡ ላይ ፡ የበዛውን ፡ ምህረቱን ፡ ስቆጥር (፪x)
ፍቅርና ፡ ምህረቱ ፡ ከቶ ፡ ገደብ ፡ የለው (፪x)
ይህን ፡ ኢየሱሴን ፡ ነፍሴ ፡ ወደደችው (፪x)

አዝ፦ ከወይን ፡ ጠጅ ፡ ይልቅ ፡ ፍቅሩ ፡ አጥግቦኛል
እኔስ ፡ ሌላ ፡ አልሻም ፡ ኢየሱስ ፡ ይበቃኛል (፪x)