ተመስገን (Temesgen) - ግሩም ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ግሩም ፡ ታደሰ
(Girum Tadesse)

Girum Tadesse 3.jpg


(3)

ከልቤ ፡ የፈለቀ
(Kelebie Yefeleqe)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የግሩም ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Girum Tadesse)

 
መከራን ፡ ባየሁበት ፡ ምድር
በገፉኝ ፡ ሰዎች ፡ ልከበር
ታሪኬን ፡ ከገለበጥከው
ልቤን ፡ ደስ ፡ ካሰኘኸው

ምሥጋናዬን ፡ ይኸው ፡ በፊትህ
እንዳከበርከኝ ፡ ላከብርህ
ያለኝም ፡ ይኸው ፡ ነውና
አንተው ፡ ከሰጠኸኝ ፡ ሌላ ፡ አሃሃ
አንተው ፡ ከሰጠኸኝ ፡ ሌላ

አዝ፦ ተመስገን ፡ ጌታ ፡ ተመስገን
ተመስገን ፡ ተመስገን (፪x)

በምሽት ፡ በሬ ፡ ሲንኳኳ
መች ፡ መሰለኝ ፡ የምትመጣ
ለካ ፡ ከሩቅ ፡ ተመልክተህ
አስተዳዳሬ ፡ የአላማረህ

አንተው ፡ ነህ ፡ የተጠጋኸኝ
አስፈሪውን ፡ ሌት ፡ ያሳለፍከኝ
ከብሬን ፡ ከደጄ ፡ አፍስሰህ
ጠረኔን ፡ ለወጥክ ፡ አጣፍጠህ ፡ አህህ
ጠረኔን ፡ ለወጥክ ፡ አጣፍጠህ

አዝ፦ ተመስገን ፡ ጌታ ፡ ተመስገን
ተመስገን ፡ ተመስገን (፪x)

ምሥጋናዬን ፡ ከወደድከው
ስሰዋውም ፡ ካሸተትከው
ከቃዬል ፡ መስዋዕት ፡ ካስበለጥከው
ለአንተ ፡ ስሰዋ ፡ ውላለሁ

ቀጥ ፡ ብሎ ፡ ወደላይ ፡ ይውጣ
አርጐ ፡ በፊትህ ፡ ጌታ
ደስ ፡ የሚያሰኝህ ፡ ምሥጋና
ይሽተት ፡ ማደሪያህ ፡ ይግባና
አሜን ፡ ይሽተት ፡ ማደሪያህ ፡ ይግባና

አዝ፦ ተመስገን ፡ ጌታ ፡ ተመስገን
ተመስገን ፡ ተመስገን (፪x)