መድሃኒቴ (Medhanitie) - ግሩም ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ግሩም ፡ ታደሰ
(Girum Tadesse)

Girum Tadesse 3.jpg


(3)

ከልቤ ፡ የፈለቀ
(Kelebie Yefeleqe)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የግሩም ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Girum Tadesse)

 
አዝ፦ መድሃኒቴ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ያረገው (ያረገው)
እንደገና ፡ ስሙን ፡ ላክብረው
ውለታው ፡ ለእኔ ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x)

ሰው ፡ ወዳጁን ፡ ቢወድ ፡ ለጥቂቱ ፡ ነው
ጥቅሙም ፡ ሲቀር ፡ ፍቅሩም ፡ ቀሪ ፡ ነው
እኔ ፡ ግን ፡ ጠላትህ ፡ ሳለሁ ፡ ወደድከኝ
በዘለዓለም ፡ ፍቅርህ ፡ ኢየሱስ ፡ አሰብከኝ

አዝ፦ መድሃኒቴ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ያረገው (ያረገው)
እንደገና ፡ ስሙን ፡ ላክብረው
ውለታው ፡ ለእኔ ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x)

መንገድ ፡ ላይ ፡ ወድቄ ፡ ጠላቴ ፡ አቁስሎኝ
ማንም ፡ አልነበረም ፡ ከውድቀት ፡ ያነሳኝ
ዘይትን ፡ አፍስሦ ፡ ቁስሎቼን ፡ የቀባኝ
እንደ ፡ ኢየሱሴ ፡ የለኝም ፡ አዳኝ

አዝ፦ መድሃኒቴ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ያረገው (ያረገው)
እንደገና ፡ ስሙን ፡ ላክብረው
ውለታው ፡ ለእኔ ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x)

ድካም ፡ ችግሬን ፡ የምትሸፍንልኝ
ምርኩዝ ፡ ድጋፌም ፡ ጋሻም ፡ የሆንከኝ
ከእናት ፡ ከአባቴም ፡ የምትበልጥብኝ
መድሃኔቴ ፡ ሆይ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ

አዝ፦ መድሃኒቴ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ያረገው (ያረገው)
እንደገና ፡ ስሙን ፡ ላክብረው
ውለታው ፡ ለእኔ ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x)

አንድ ፡ ሁለት ፡ ብዬ ፡ ቁጥር ፡ ብሰጠው
ጌታ ፡ ውለታህ ፡ ከልክ ፡ በላይ ፡ ነው
እንደ ፡ እኔ ፡ ውለታው ፡ የበዛባችሁ
ቅኔን ፡ ተቀኙለት ፡ እልል ፡ ብላችሁ

አዝ፦ መድሃኒቴ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነው (ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነው)
ለእኔ ፡ ያረገው (ያረገው)
እንደገና ፡ ስሙን ፡ ላክብረው (ስሙን ፡ ላክብረው)
ውለታው ፡ ለእኔ ፡ ብዙ ፡ ነው (ለእኔ ፡ ብዙ ፡ ነው) (፪x)

ዕልልታ!