በዘለዓለም ፡ ዙፋን ፡ ላይ (Bezelealem Zufan Lay) - ግሩም ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ግሩም ፡ ታደሰ
(Girum Tadesse)

Girum Tadesse 3.jpg


(3)

ከልቤ ፡ የፈለቀ
(Kelebie Yefeleqe)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የግሩም ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Girum Tadesse)

 
አዝ፦ በዘለዓለም ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ተቀምጠህ ፡ ያለህ
በሰማይም ፡ በምድርም ፡ ሙሉ ፡ ስልጣን ፡ ያለህ
ዙፋንህ ፡ ተነቃንቆ ፡ ተገርስሶ ፡ የታለ
እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ (፪x)

ዘንዶውን ፡ ገጥመህ ፡ ያሸነፍክ ፡ ጌታ
በሃይል ፡ በስልጣን ፡ የምትበረታ
ጽኑ ፡ ሃያላንን ፡ ሁሉ ፡ ያሸነፍክ
የሃያል ፡ ሃያል ፡ ኢየሱስ ፡ ብርቱ ፡ ነህ

አዝ፦ በዘለዓለም ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ተቀምጠህ ፡ ያለህ
በሰማይም ፡ በምድርም ፡ ሙሉ ፡ ስልጣን ፡ ያለህ
ዙፋንህ ፡ ተነቃንቆ ፡ ተገርስሶ ፡ የታለ
እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ

ሰማይ ፡ ምድርን ፡ በስልጣንህ ፡ ቃል
ፍጥረት ፡ እስኪደነቅ ፡ ሰርተሃቸዋል
ስላልተገኘልህ ፡ ከቶ ፡ ለአንተ ፡ አቻ
ስምህ ፡ ገነነ ፡ እስከምድር ፡ ዳርቻ

አዝ፦ በዘለዓለም ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ተቀምጠህ ፡ ያለህ
በሰማይም ፡ በምድርም ፡ ሙሉ ፡ ስልጣን ፡ ያለህ
ዙፋንህ ፡ ተነቃንቆ ፡ ተገርስሶ ፡ የታለ
እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ

ሃይልህ ፡ ከሃያላን ፡ ሁሉ ፡ ይበልጣል
ውሃን ፡ እንደግምብ ፡ ቀጥ ፡ አድርጐ ፡ ያቆማል
ከአጥፊዎችም ፡ እጅ ፡ ክንድህ ፡ ያስጥላል
የይሁዳ ፡ አምበሳ ፡ ማን ፡ ይመስልሃል

አዝ፦ በዘለዓለም ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ተቀምጠህ ፡ ያለህ
በሰማይም ፡ በምድርም ፡ ሙሉ ፡ ስልጣን ፡ ያለህ
ዙፋንህ ፡ ተነቃንቆ ፡ ተገርስሶ ፡ የታለ
እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ

ሃይልህን ፡ ሳያውቁ ፡ የተነሱብህ
አስከትተው ፡ ጦር ፡ የዘመቱብህ
ክንድህ ፡ ገጥሟቸው ፡ ተሸንፈዋል
ስማቸው ፡ ጠፍቶ ፡ አንተ ፡ ነግሰሃል

አዝ፦ በዘለዓለም ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ተቀምጠህ ፡ ያለህ
በሰማይም ፡ በምድርም ፡ ሙሉ ፡ ስልጣን ፡ ያለህ
ዙፋንህ ፡ ተነቃንቆ ፡ ተገርስሶ ፡ የታለ
እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ

ሰማይ ፡ ምድርን ፡ በስልጣንህ ፡ ቃል
ፍጥረት ፡ እስኪደነቅ ፡ ሰርተሃቸዋል
ስላልተገኘልህ ፡ ከቶ ፡ ለአንተ ፡ አቻ
ስምህ ፡ ገነነ ፡ እስከምድር ፡ ዳርቻ

አዝ፦ በዘለዓለም ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ተቀምጠህ ፡ ያለህ
በሰማይም ፡ በምድርም ፡ ሙሉ ፡ ስልጣን ፡ ያለህ
ዙፋንህ ፡ ተነቃንቆ ፡ ተገርስሶ ፡ የታለ
እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ (፪x)