አንድ ፡ ነገር ፡ የምፈራው (And Neger Yemeferaw) - ግሩም ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ግሩም ፡ ታደሰ
(Girum Tadesse)

Girum Tadesse 3.jpg


(3)

ከልቤ ፡ የፈለቀ
(Kelebie Yefeleqe)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የግሩም ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Girum Tadesse)

 
አዝ፦ አንድ ፡ ነገር ፡ በሕይወቴ ፡ የምፈራው
አንተ ፡ ዝም ፡ ስትለኝ ፡ ነው (፪x)
አንድ ፡ ነገር ፡ በሕይወቴ ፡ የምሰጋው
አንተ ፡ ዝም ፡ ስትለኝ ፡ ነው (፪x)
እባክህ ፡ ተናገረኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ዝም ፡ አትበለኝ

ሁሉን ፡ ወደምትችል ፡ ወደአንተ ፡ እጮሃለሁ
ልትረዳኝ ፡ እንደምትችል ፡ ይህንን ፡ አውቃለሁ
በወደድከው ፡ መንገድ ፡ ጌታ ፡ ተናገረኝ
ብቻ ፡ አንድ ፡ ነገር ፡ ኢየሱስ ፡ ዝም ፡ አትበለኝ
ብቻ ፡ አንድ ፡ ነገር ፡ አባ ፡ ዝም ፡ አትበለኝ

አዝ፦ አንድ ፡ ነገር ፡ በሕይወቴ ፡ የምፈራው
አንተ ፡ ዝም ፡ ስትለኝ ፡ ነው (፪x)
አንድ ፡ ነገር ፡ በሕይወቴ ፡ የምሰጋው
አንተ ፡ ዝም ፡ ስትለኝ ፡ ነው (፪x)
እባክህ ፡ ተናገረኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ዝም ፡ አትበለኝ

ሙግቴ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ መሆኑን ፡ ስታውቀው
ለምን ፡ ዝም ፡ እንዳልከኝ ፡ ያልገባኝ ፡ ሚስጥር ፡ ነው
ተናገረኝ ፡ ጌታ ፡ ያየኸው ፡ ጉድለቴን
አንተ ፡ ዝም ፡ ካልክማ ፡ ሌላ ፡ ማነው ፡ ያለኝ
አንተ ፡ ዝም ፡ ካልክማ ፡ ሌላ ፡ ማንም ፡ የለኝ

አዝ፦ አንድ ፡ ነገር ፡ በሕይወቴ ፡ የምፈራው
አንተ ፡ ዝም ፡ ስትለኝ ፡ ነው (፪x)
አንድ ፡ ነገር ፡ በሕይወቴ ፡ የምሰጋው
አንተ ፡ ዝም ፡ ስትለኝ ፡ ነው (፪x)
እባክህ ፡ ተናገረኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ዝም ፡ አትበለኝ


አንተ ፡ ዝም ፡ ባልክበት ፡ በካህኑ ፡ ኤሊ ፡ ዘመን
ድል ፡ አይታወቅም ፡ ሁሌ ፡ መሸነፍ ፡ ነው
እስከ ፡ ሲዖል ፡ ድረስ ፡ ነፍስን ፡ ያወርዳታል
የአንተ ፡ ዝምታ ፡ ነፍሴን ፡ ያሰጋታል (፪x)

አዝ፦ አንድ ፡ ነገር ፡ በሕይወቴ ፡ የምፈራው
አንተ ፡ ዝም ፡ ስትለኝ ፡ ነው (፪x)
አንድ ፡ ነገር ፡ በሕይወቴ ፡ የምሰጋው
አንተ ፡ ዝም ፡ ስትለኝ ፡ ነው (፪x)
እባክህ ፡ ተናገረኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ዝም ፡ አትበለኝ

መልሰህ ፡ መላልሰህ ፡ ብትናገረኝም
ማስተዋል ፡ ቢያቅተኝ ፡ ተው ፡ አትሰልቸኝ
በአባትነት ፡ ፍቅርህ ፡ በልምጭ ፡ ሾጥ ፡ አርገኝ
ዝም ፡ ካልከኝማ ፡ አባ ፡ ዋጋም ፡ የለኝ
ዝም ፡ ካልከኝማ ፡ ኢየሱስ ፡ ዋጋም ፡ የለኝ

አዝ፦ አንድ ፡ ነገር ፡ በሕይወቴ ፡ የምረካው
አንተ ፡ ስትናገረኝ ፡ ነው (፪x)
አንድ ፡ ነገር ፡ በሕይወቴ ፡ የምፈታው
አንተ ፡ ስትናገረኝ ፡ ነው (፪x)
እባክህ ፡ ተናገረኝ ፡ እለመልማለሁ