From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ ሲነጋ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ
ሲመሽም ፡ ኢየሱስ ፡ የሚያሰኝ
በፍቅር ፡ ነፍስን ፡ ይዞ ፡ የሚያስቀር
ኧረ ፡ አለህ ፡ አለህ ፡ ልዩ ፡ ነገር (፪x)
እጅህን ፡ አንተ ፡ ስትዘረጋ
ይጠግባል ፡ ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ በአንተ
ደግነት ፡ ቸርነት ፡ ስምህ ፡ ነው
አትጥልም ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ ሲል ፡ ሰው (፪x)
አዝ፦ ሲነጋ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ
ሲመሽም ፡ ኢየሱስ ፡ የሚያሰኝ
በፍቅር ፡ ነፍስን ፡ ይዞ ፡ የሚያስቀር
ኧረ ፡ አለህ ፡ አለህ ፡ ልዩ ፡ ነገር
ቀን ፡ መሽቶ ፡ ለጨለመበት ፡ ሰው
እረፍትን ፡ እፎይታን ፡ ምጸጠው
በሞተው ፡ ባበቃ ፡ ነገር ፡ ላይ
ትንሳኤ ፡ ሕይወትን ፡ ምታሳይ
አዝ፦ ሲነጋ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ
ሲመሽም ፡ ኢየሱስ ፡ የሚያሰኝ
በፍቅር ፡ ነፍስን ፡ ይዞ ፡ የሚያስቀር
ኧረ ፡ አለህ ፡ አለህ ፡ ልዩ ፡ ነገር (፪x)
|