ማንንም ፡ አይጥልም (Manenem Aytelem) - ጌታቸው ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታቸው ፡ ታደሰ
(Getachew Tadesse)

Getachew Tadesse 2.png


(2)

እኔ ፡ ያልዘመርኩኝ ፡ ማን ፡ ይዘምር
(Enie Yalzemerkugn Man Yezemer)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2003)
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታቸው ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Getachew Tadesse)

አዝ፦ ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ስማኝ
ዛሬም ፡ እነግርሃለሁኝ
ብወድቅ ፡ እነሣለሁኝ
በጨለማ ፡ ብቀመጥም ፡ እንኳን
እግዚአብሔር ፡ ብርሃን ፡ ይሆንልኛል
እርሱ ፡ ወጥመድህን ፡ ይቆርጥልኛል
አይምሰልህ ፡ ለዘለዓለም
አምላኬ ፡ ማንንም ፡ አይጥልም
ለዘለዓለም ፡ አምላኬ ፡ ማንንም ፡ አይጥልም

በድካሜ ፡ የሚራራልኝ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ስላለልኝ
ወደ ፡ ብርሃን ፡ ያወጣል ፡ ክብሩን ፡ በግልጽ ፡ ያሳየኛል
ሁለቴም ፡ ባይንሽ ፡ ታያለሽ ፡ በዕፍረት ፡ ትከደኛለሽ
ትረገጭ ፡ እንደ ፡ ጭቃ ፡ ይህ ፡ ሊሆን ፡ ግድ ፡ ነው ፡ በቃ

አዝ፦ ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ስማኝ
ዛሬም ፡ እነግርሃለሁኝ
ብወድቅ ፡ እነሣለሁኝ
በጨለማ ፡ ብቀመጥም ፡ እንኳን
እግዚአብሔር ፡ ብርሃን ፡ ይሆንልኛል
እርሱ ፡ ወጥመድህን ፡ ይቆርጥልኛል
አይምሰልህ ፡ ለዘለዓለም
አምላኬ ፡ ማንንም ፡ አይጥልም
ለዘለዓለም ፡ አምላኬ ፡ ማንንም ፡ አይጥልም

ሙሴ ፡ እናቱ ፡ ስትጥለው ፡ የምታደርገው ፡ ነገር ፡ ጠፍቶ
መወሸቂያ ፡ መደበቂያ ፡ የሚሆን ፡ ሥፍራ ፡ ለርሱ ፡ ታጥቶ
እግዚአብሔር ፡ ግን ፡ ተቀበለው ፡ ከእጇ ፡ ሥር ፡ ወስዶ ፡ አቀፈው
የተፈራ ፡ ቤት ፡ ሊያኖረው ፡ ክብሩን ፡ በግል ፡ እያሳየው

አዝ፦ ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ስማኝ
ዛሬም ፡ እነግርሃለሁኝ
ብወድቅ ፡ እነሣለሁኝ
በጨለማ ፡ ብቀመጥም ፡ እንኳን
እግዚአብሔር ፡ ብርሃን ፡ ይሆንልኛል
እርሱ ፡ ወጥመድህን ፡ ይቆርጥልኛል
አይምሰልህ ፡ ለዘለዓለም
አምላኬ ፡ ማንንም ፡ አይጥልም
ለዘለዓለም ፡ አምላኬ ፡ ማንንም ፡ አይጥልም

መች ፡ ይጥላል ፡ የእኔ ፡ ጌታ?
ያነሣል ፡ ወደ ፡ ከፍታ
ለጠበቀው ፡ ለታገሰው
የሚያኮራ ፡ ምላሽ ፡ አለው

አዝ፦ ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ስማኝ
ዛሬም ፡ እነግርሃለሁኝ
ብወድቅ ፡ እነሣለሁኝ
በጨለማ ፡ ብቀመጥም ፡ እንኳን
እግዚአብሔር ፡ ብርሃን ፡ ይሆንልኛል
እርሱ ፡ ወጥመድህን ፡ ይቆርጥልኛል
አይምሰልህ ፡ ለዘለዓለም
አምላኬ ፡ ማንንም ፡ አይጥልም
ለዘለዓለም ፡ አምላኬ ፡ ማንንም ፡ አይጥልም