ለዚህ ፡ ያደረስከኝ (Lezih Yadereskegn) - ጌታቸው ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታቸው ፡ ታደሰ
(Getachew Tadesse)

Getachew Tadesse 2.png


(2)

እኔ ፡ ያልዘመርኩኝ ፡ ማን ፡ ይዘምር
(Enie Yalzemerkugn Man Yezemer)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2003)
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታቸው ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Getachew Tadesse)

ጌታዬ ፡ ለዚህ ፡ ያደረስኸኝ ፡ እኔ ፡ ማን ፡ ነኝ?
ጌታዬ ፡ ለዚህ ፡ ያበቃኸኝ ፡ እኔ ፡ ማን ፡ ነኝ?

ከየት ፡ ነው ፡ የመጣሁት ፡ ያነሳኸኝ ፡ ጌታ?
የበግ ፡ ኮቴ ፡ ስከተል ፡ ነበር ፡ ጥዋት ፡ ማታ
ከሳኦል ፡ ከፍልስጥኤም ፡ ከአማሌቅ ፡ ሁሉ
ተርፌአለሁ ፡ የአንተ ፡ ጋሻነት ፡ በመኖሩ

አሁንም ፡ እባብ ፡ ጊንጡን ፡ ረግጬ ፡ እኖራለሁ
በዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ስምህን ፡ እባርካለሁ

አንደበቴ ፡ ተከፍቶ ፡ ዛሬ ፡ እናገራለሁ
ሽባነቴም ፡ ቀርቶ ፡ እንደልብ ፡ እራመዳለሁ
ያሰሩኝ ፡ የገዙኝ ፡ አጋንንት ፡ ለሞቴ
ጥለው ፡ ሸሹ ፡ ጌታዬ ፡ አንተን ፡ ሲያዩ ፡ በሕይወቴ

ምንም ፡ የለም ፡ ከታሰርኩት ፡ ሁሉ ፡ ተፈትቻለሁ
ዘመኔን ፡ አንተን ፡ ክበር ፡ እያልኩ ፡ እኖራለሁ

ጠላቶቼንም ፡ ከእግሮቼ ፡ በታች ፡ አስገዝተሃል
ዘንዶውን ፡ በስለታም ፡ ሰይፍህ ፡ አንተ ፡ ወግተሃል
እባብ ፡ ጊንጥን ፡ ልረግጥ ፡ ብቻ ፡ አይደለም ፡ የእኔ ፡ ድርሻ
ልኖር ፡ ነው ፡ በቤትህ ፡ ሳመልክህ ፡ እስከመጨረሻ

ሳስበው ፡ ይህ ፡ ብቻ ፡ አይደለም ፡ ደስታዬ
ጥልቅ ፡ ነው ፡ የእኔን ፡ ፍቅር ፡ ለአንተ ፡ መግለጫዬ

ይበቃኛል ፡ አሁንም ፡ ከአንተው ፡ ጋር ፡ እስማማለሁ
አልማዝ ፡ ዕንቁ ፡ ጣኦቴን ፡ ከድንኳን ፡ አርቃለሁ
የኦፊር ፡ ወርቄን ፡ በጅረት ፡ ድንጋይ ፡ ውስጥ ፡ ልጥል