ልዩ ፡ ነህ (Leyu Neh) - ጌታቸው ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታቸው ፡ ታደሰ
(Getachew Tadesse)

Getachew Tadesse 2.png


(2)

እኔ ፡ ያልዘመርኩኝ ፡ ማን ፡ ይዘምር
(Enie Yalzemerkugn Man Yezemer)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2003)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታቸው ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Getachew Tadesse)

አንተ ፡ እኮ ፡ ለእኔ ፡ ጌታ ፡ ነህ
አንተ ፡ እኮ ፡ ለእኔ ፡ ልዩ ፡ ነህ
አንተ ፡ እኮ ፡ ለእኔ ፡ ወዳጄ ፡ ነህ

ሥሜን ፡ በሰማዩ ፡ መዝገብ ፡ መቀመጫዬን ፡ በአብ ፡ ቀኝ
እረፍትን ፡ ለዘለዓለም ፡ ለዘመኔም ፡ ቁጥር ፡ የለም
ስሄድ ፡ በመላዕክት ፡ ታጅቤ ፡ እኔም ፡ በአምላኬ ፡ ታስቤ
ሰማያት ፡ ደስ ፡ እያላቸው ፡ እኔ ፡ መዳኔ ፡ ገርሟቸው

በትውልድ ፡ ላላገኘሁት
በትምህርት ፡ በዕውቀት ፡ በችሎታ
የማያልፍ ፡ ክብር ፡ አውራሼ
ልዩ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ የእኔ ፡ ጌታ

ልዩ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነህ
ልዩ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔስ ፡ ልዩ ፡ ነህ

ስለጥበቃህ ፡ አልሰጋም ፡ ተጠብቄ ፡ አይቻለሁ
ስለማዳንህ ፡ ብናገር ፡ አለኝ ፡ ብዙ ፡ አወራለሁ
አባትነትህማ ፡ ለእኔ ፡ ሆኖኝ ፡ ጧት ፡ ማታ ፡ ትዝታ
እኖራለሁ ፡ ተደስቼ ፡ በአንተ ፡ በአስደናቂ ፡ ጌታ

በዘመድ ፡ አልታመንም
ዛሬ ፡ ታይቶ ፡ በሚጠወልግ
ብሩንም ፡ አይቼዋለሁ
እንደ ፡ ጉድፍ ፡ ቆጥሬዋለሁ
በምንም ፡ የማይገመት ፡ ሀብቴ
ትምክህቴ ፡ ልዩ ፡ ኩራቴ
የሕይወት ፡ ዘመን ፡ ምርጫዬ
አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔስ ፡ ጌታዬ

ማንም ፡ ላይገዛኝ ፡ ኖራለሁ ፡ ሁሉን ፡ በአንተ ፡ አሸንፌአለሁ
የሚገዛኝ ፡ በዚህ ፡ ዓለም ፡ ከአንተ ፡ ውጭ ፡ ማንም ፡ የለም
ገንዘብ ፡ ሀብት ፡ ዕውቀት ፡ ንብረት ፡ በዚህ ፡ ዓለም ፡ ነገር ፡ መጠመድ
አበቃ ፡ አከተመለት ፡ ከአንተ ፡ የተገናኘን ፡ ዕለት