ከምልህ ፡ በላይ ፡ ነህ (Kemeleh Belay Neh) - ጌታቸው ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታቸው ፡ ታደሰ
(Getachew Tadesse)

Getachew Tadesse 2.png


(2)

እኔ ፡ ያልዘመርኩኝ ፡ ማን ፡ ይዘምር
(Enie Yalzemerkugn Man Yezemer)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2003)
ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታቸው ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Getachew Tadesse)

ኤልሻዳይ ፡ ብዬ ፡ ዘምሬአለሁ
ጌታም ፡ ነህ ፡ ብዬ ፡ መስክሬአለሁ
አሁን ፡ ግን ፡ ቃላትን ፡ ስላጣሁ
ከምለው ፡ በላይ ፡ ነህ ፡ ብያለሁ
ከምልህ ፡ በላይ ፡ ጌታ (፫x) ፡ ነህ
የእኔ ፡ ቃላት ፡ የማይገልጽህ ፡ የሰው ፡ ቃላት
ከምልህ ፡ በላይ ፡ ጌታ ፡ ነህ

እኔን ፡ አሳፍሮኝ ፡ አያውቅም ፡ የማገለግለው ፡ ጌታ
ያኖረኛል ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ጠላቶቼን ፡ እየመታ
ለምን ፡ ይህን ፡ አደረግህ? ብሎ ፡ የጠየቀው ፡ የለም
ሥልጣኑ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ጉልበቱ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው

እሠይ (፮x)
ጌታ ፡ ነው ፡ በምድር ፡ በሰማይ
ከሁሉም ፡ በላይ
ነው ፡ ኢየሱስ ፡ በምድር ፡ በሰማይ
ከሁሉም ፡ በላይ

ስለ ፡ በደሌ ፡ ዝቅ ፡ ብሎ ፡ መስቀል ፡ ተሸክም ፡ ያየው ፡ ሰው
የሰማይ ፡ የምድር ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ብሎ ፡ ማን ፡ ይገምተው?
ቢሆንም ፡ ተነሥቶ ፡ ጌታ ፡ በዓብ ፡ ቀኝ ፡ ተቀምጧል
በሰማይና ፡ በምድር ፡ ሁሉን ፡ አንበርክኳል

ግንበኞች ፡ የናቁት ፡ ድንጋይ ፡ እርሱ ፡ የማዕዘን ፡ ራስ ፡ ሆነ
አይጠቅምም ፡ ብለው ፡ የጣሉት ፡ የትንሣዔ ፡ ጌታ ፡ ሆነ
የናቁትን ፡ አሳፍሮ ፡ እጅ ፡ አስጭኗቸዋል
በመንግሥቱም ፡ እያበራ ፡ ዘለዓለም ፡ ይኖራል