ክብሩ ፡ ለአንተ (Kebru Lante) - ጌታቸው ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታቸው ፡ ታደሰ
(Getachew Tadesse)

Getachew Tadesse 2.png


(2)

እኔ ፡ ያልዘመርኩኝ ፡ ማን ፡ ይዘምር
(Enie Yalzemerkugn Man Yezemer)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2003)
ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታቸው ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Getachew Tadesse)

አዝ፦ ክብሩ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ ፡ መድኃኒቴ
ከውስጥም ፡ ከውጭም ፡ ሰላም ፡ ሞላ ፡ ቤቴ
ተመስገን ፡ ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ
አንተን ፡ በማግኘቴ ፡ እኔም ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ
ስምህን ፡ እየጠራሁ ፡ እባርክሃለሁ
ስንቱን ፡ በአንተ ፡ አልፌ ፡ ለዚህ ፡ ደርሻለሁ

ከዓለም ፡ ወጣሁና ፡ ምን ፡ ይቀርብኛል?
ይመስገን ፡ ጌታዬ ፡ ሁሉ ፡ ሞልቶልኛል
በግርፋት ፡ ቁስሉ ፡ እርሱ ፡ ፈውሷታል
ነፍሴም ፡ ከዚህ ፡ ውጭ ፡ ምን ፡ ያስፈልጋታል?
ከዚህ ፡ የተሻለ ፡ ምን ፡ ለውጥ ፡ ሊያመጣልኝ
የሚለኝ ፡ ጠላቴ ፡ ርስትህን ፡ ለውጠኝ

አዝ፦ ክብሩ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ ፡ መድኃኒቴ
ከውስጥም ፡ ከውጭም ፡ ሰላም ፡ ሞላ ፡ ቤቴ
ተመስገን ፡ ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ
አንተን ፡ በማግኘቴ ፡ እኔም ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ
ስምህን ፡ እየጠራሁ ፡ እባርክሃለሁ
ስንቱን ፡ በአንተ ፡ አልፌ ፡ ለዚህ ፡ ደርሻለሁ

ራሴን ፡ ስመለከት ፡ ለዚህ ፡ የማልበቃ
እንዴት ፡ ተደባለቁ ፡ ከአንተ ፡ ቅዱስ ፡ መንጋ?
ርስትህን ፡ አወረስኸኝ ፡ ከቅዱሣን ፡ ጋራ
ከአንተ ፡ ጋር ፡ አኖርኸኝ ፡ ሰማያዊ ፡ ሥፍራ
ምሕረትህ ፡ ደርሶኛል ፡ ለዚህ ፡ በቅቻለሁ
እኔም ፡ በዘመኔ ፡ እገዛልሃለሁ

አዝ፦ ክብሩ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ ፡ መድኃኒቴ
ከውስጥም ፡ ከውጭም ፡ ሰላም ፡ ሞላ ፡ ቤቴ
ተመስገን ፡ ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ
አንተን ፡ በማግኘቴ ፡ እኔም ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ
ስምህን ፡ እየጠራሁ ፡ እባርክሃለሁ
ስንቱን ፡ በአንተ ፡ አልፌ ፡ ለዚህ ፡ ደርሻለሁ

ታስሬ ፡ አግኝተህ ፡ ነው ፡ አንተ ፡ ያስፈታኸኝ
እኔም ፡ ነጻ ፡ ወጣሁ ፡ ጌታ ፡ ስላሰብኸኝ
ስለ ፡ እኔ ፡ የሚጠይቅ ፡ አጭር ፡ መልስ ፡ ያገኛል
ትዕዛዝን ፡ ሰጥተህ ፡ ነው ፡ ብለህ ፡ ያስፈልገኛል
ክብርን ፡ አለበስኸኝ ፡ ውርደቴ ፡ ቀረና
ተገረመ ፡ ሁሉም ፡ መዳኔን ፡ አየና

አዝ፦ ክብሩ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ ፡ መድኃኒቴ
ከውስጥም ፡ ከውጭም ፡ ሰላም ፡ ሞላ ፡ ቤቴ
ተመስገን ፡ ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ
አንተን ፡ በማግኘቴ ፡ እኔም ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ
ስምህን ፡ እየጠራሁ ፡ እባርክሃለሁ
ስንቱን ፡ በአንተ ፡ አልፌ ፡ ለዚህ ፡ ደርሻለሁ

የማመልክህ ፡ አምላክ ፡ ጊዜያዊ ፡ አይደለም
ትላንትና ፡ የሌለህ ፡ ዓለም ፡ የማታውቅህ
አይደለም ፡ ጌታዬ ፡ ታሪክ ፡ ያፈለቀህ
ለዚህች ፡ ዓለም ፡ እንኳ ፡ ራስህ ፡ መድኃኒት ፡ ነህ
ለጠየቀኝ ፡ ሁሉ ፡ ለመልስ ፡ ዝግጁ ፡ ነኝ
ውዴ ፡ መድኃኒቴ ፡ እኔን ፡ እንዳዳንኸኝ

አዝ፦ ክብሩ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ ፡ መድኃኒቴ
ከውስጥም ፡ ከውጭም ፡ ሰላም ፡ ሞላ ፡ ቤቴ
ተመስገን ፡ ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ
አንተን ፡ በማግኘቴ ፡ እኔም ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ
ስምህን ፡ እየጠራሁ ፡ እባርክሃለሁ
ስንቱን ፡ በአንተ ፡ አልፌ ፡ ለዚህ ፡ ደርሻለሁ