ፍቅርህ ፡ ልዩ ፡ ነው (Feqreh Leyu New) - ጌታቸው ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታቸው ፡ ታደሰ
(Getachew Tadesse)

Getachew Tadesse 2.png


(2)

እኔ ፡ ያልዘመርኩኝ ፡ ማን ፡ ይዘምር
(Enie Yalzemerkugn Man Yezemer)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2003)
ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታቸው ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Getachew Tadesse)

አዝ፦ ፍቅርህ ፡ ልዩ ፡ ነው (፬x)

ትላንትን ፡ አይቼህ ፡ ዛሬም
የማትለወጥ ፡ ለዘለዓለም
ኢየሱስን ፡ አየሁ ፡ የነፍስ ፡ ወዳጅ
ፍቅርህ ፡ ለዘለዓለምም ፡ የማያረጅ

አዝ፦ ፍቅርህ ፡ ልዩ ፡ ነው (፬x)

ይሸከማል ፡ እርሱ ፡ እስከ ፡ ሽበት
አይሰለችም ፡ እስከ ፡ ሽምግልና
የጠራውን ፡ ያውቃል ፡ ያጸናዋል
ይመራዋል ፡ በክብር ፡ ጐዳና

አዝ፦ ፍቅርህ ፡ ልዩ ፡ ነው (፬x)

የማይታለፉትን ፡ ቀናት
አለፍኳቸው ፡ በአንተ ፡ ብርታት
ዛሬ ፡ ፀሐይ ፡ ወጥቶልኛል
በአንተ ፡ ብዙ ፡ ሆኖልኛል

አዝ፦ ፍቅርህ ፡ ልዩ ፡ ነው (፬x)