እኔ ፡ ያልዘመርኩኝ (Enie Yalzemerkugn) - ጌታቸው ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታቸው ፡ ታደሰ
(Getachew Tadesse)

Getachew Tadesse 2.png


(2)

እኔ ፡ ያልዘመርኩኝ ፡ ማን ፡ ይዘምር
(Enie Yalzemerkugn Man Yezemer)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2003)
ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታቸው ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Getachew Tadesse)

እኔ ፡ ያልዘመርኩ ፡ ማን ፡ ይዘምር?
ለኢየሱሴ ፡ ሥሙ ፡ ክብር
ስንቴ ፡ ከሞት ፡ አምልጫለሁ?
ሲታደገኝ ፡ አይቻለሁ
እንደ ፡ እኔ ፡ ምሕረት ፡ የበዛለት
ምሥጋናውን ፡ ይሰዋለት

የታሪኬ ፡ ጅማሬና ፡ የፍጻሜ ፡ መደምደሚያው
በሕይወቴ ፡ ሥፍራ ፡ ያለው ፡ አንድ ፡ ቁጥር ፡ ለኢየሱስ ፡ ነው
በቁልምጫ ፡ የምጠራው ፡ ፍቅሩ ፡ ልቤን ፡ ነክቶት ፡ ነው

በደም ፡ ተለውሼ ፡ ሲያየን ፡ ፊቱን ፡ ዞሮ ፡ ያላለፈኝ
ጠርቶ ፡ በሕይወት ፡ ኑር ፡ ያለኝ ፡ ምሕረቱን ፡ ያበዛልኝ
እንደ ፡ እኔ ፡ ማን ፡ አለና ፡ ነው? ከማመስገን ፡ የምዘገየው

ይህን ፡ ጌታ ፡ አንተ ፡ አምላኬ ፡ ነህ ፡ አልኩት
አምላኬ ፡ ነህ ፡ አልኩት

መንገድ ፡ ዳር ፡ ወድቄ ፡ ሲያየኝ ፡ ራርቶ ፡ በፍቅር ፡ ያኖረኝ
ቸርነቱ ፡ በዝቶ ፡ እስኪታይ ፡ ሰማይን ፡ ከፍቶ ፡ በእኔ ፡ ላይ
ወደ ፡ ራሱ ፡ ስላስጠጋኝ ፡ እንዳልዘምር ፡ ማነው ፡ ከልካይ?

ይህን ፡ ጌታ ፡ አንተ ፡ አምላኬ ፡ ነህ ፡ አልኩት
አምላኬ ፡ ነህ ፡ አልኩት
በዘመኔ ፡ ብዙ ፡ ነገር ፡ አይቻለሁ

እግዚአብሔርን ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ ብዬዋለሁ
ባሕር ፡ ከፍሎ ፡ ሲያሻግረኝ ፡ ዓይኔ ፡ አይቶታል
እግዚአብሔርን ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ ብሎታል
በዘመኔ ፡ ብዙ ፡ ነገር ፡ አይቻለሁ
እግዚአብሔርን ፡ ፍቅር ፡ ነህ ፡ ብዬዋለሁ
ሲሸከመኝ ፡ ሲታገሰኝ ፡ ዓይኔ ፡ አይቶታል
እግዚአብሔርን ፡ ፍቅር ፡ ነህ ፡ ፍቅር ፡ ነህ ፡ ብሎታል