ድንቅ ፡ ነህ (Denq Neh) - ጌታቸው ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታቸው ፡ ታደሰ
(Getachew Tadesse)

Getachew Tadesse 2.png


(2)

እኔ ፡ ያልዘመርኩኝ ፡ ማን ፡ ይዘምር
(Enie Yalzemerkugn Man Yezemer)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2003)
ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታቸው ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Getachew Tadesse)

አዝድንቅ ፡ ነህ (፬x) ፡ ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነህ
ሃሌሉያ ፡ አሃ ፡ ሃ
ድንቅ ፡ ነህ (፬x)
ለእኔ ፡ ክብር ፡ ነህ

አስደናቂነትህን ፡ አይተን ፡ እስከዛሬ
እንጂ ፡ መቼ ፡ ኖርን? ሰምተን ፡ ጭፍን ፡ ወሬ
ሥራህን ፡ በሕይወታችን ፡ ተገልጦ ፡ ስላየነው
አናፍርም ፡ ያኮራል ፡ የአንተ ፡ መሆን ፡ ክብር ፡ ነው

አዝድንቅ ፡ ነህ (፬x) ፡ ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነህ
ሃሌሉያ ፡ አሃ ፡ ሃ
ድንቅ ፡ ነህ (፬x)
ለእኔ ፡ ክብር ፡ ነህ

ቃላት ፡ አጣሁ ፡ እንጂ ፡ ብዙ ፡ እናገር ፡ ነበር
ጠላት ፡ በእኔ ፡ ዘግቶ ፡ ስለከፈትክልኝ ፡ በር
ርስት ፡ አገኘሁ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በዚህ ፡ አበቃ?
በቤትህ ፡ ወግ ፡ አየሁ ፡ ቀረና ፡ ሰቆቃ

አዝድንቅ ፡ ነህ (፬x) ፡ ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነህ
ሃሌሉያ ፡ አሃ ፡ ሃ
ድንቅ ፡ ነህ (፬x)
ለእኔ ፡ ክብር ፡ ነህ

ለእኔ ፡ አጋዥ ፡ የሚሆን ፡ ጠፍቶ ፡ ዝም ፡ ሲባል
ረዳቴ ፡ ሆነኸኝ ፡ ከተፍ ፡ ብለሃል
የቀራንዮ ፡ ወዳጅ ፡ ተባረክ ፡ ዘለዓለም
የክፉ ፡ ቀን ፡ ወዳጅ ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ የለም

አዝድንቅ ፡ ነህ (፬x) ፡ ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነህ
ሃሌሉያ ፡ አሃ ፡ ሃ
ድንቅ ፡ ነህ (፬x)
ለእኔ ፡ ክብር ፡ ነህ