አንድን ፡ ነገር (Anden Neger) - ጌታቸው ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታቸው ፡ ታደሰ
(Getachew Tadesse)

Getachew Tadesse 2.png


(2)

እኔ ፡ ያልዘመርኩኝ ፡ ማን ፡ ይዘምር
(Enie Yalzemerkugn Man Yezemer)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2003)
ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታቸው ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Getachew Tadesse)

አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ አንድን ፡ ነገር ፡ ለምኜዋለሁ
ያንን ፡ ከእጁ ፡ እናፍቃለሁ

አሮጌውን ፡ በአዲስ ፡ ተክቶ
እስኪወስደኝ ፡ ጌታዬ ፡ መጥቶ
የሞተልኝ ፡ ወዳጄን ፡ እስካይ
ናፍቆቴ ፡ እስኪፈጸም ፡ በሰማይ
እንዲጠብቀኝ ፡ ምድር ፡ ላይ

አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ አንድን ፡ ነገር ፡ ለምኜዋለሁ
ያንን ፡ ከእጁ ፡ እናፍቃለሁ

በሕይወቴ ፡ ዘመን ፡ በሙሉ
ልኖር ፡ እኔም ፡ እንደ ፡ ሕያው ፡ ቃሉ
ምኞቴ ፡ ነው ፡ ይህ ፡ አንድ ፡ ነገር
እስካለሁ ፡ በዚህች ፡ ጠፊ ፡ ምድር
ይህን ፡ ነገር ፡ እናፍቃለሁ

አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ አንድን ፡ ነገር ፡ ለምኜዋለሁ
ያንን ፡ ከእጁ ፡ እናፍቃለሁ

የመምጫህን ፡ ቀን ፡ ስለማላውቅ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ የአንተን ፡ መገለጥ
ያለ ፡ ነውርና ፡ ነቀፋ
ሆኜ ፡ እንድጠብቀው ፡ በተስፋ
ይህን ፡ ነገር ፡ እናፍቃለሁ

አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ አንድን ፡ ነገር ፡ ለምኜዋለሁ
ያንን ፡ ከእጁ ፡ እናፍቃለሁ