Geja Kale Hiwot Church A Choir/Vol/Ante Eyemerahen

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

|አዝ፡ አንተ እየመራኸን እዚህ ደርሰናል ክፉውን ዘመን በአንተ አልፈናል የነገውንም ደግሞ ታውቃለህ አንተ በታምራት...ታከርመናለህ...ታኖረናለህ (×፪)

በእጃችን ያለው ጥቂት ዱቄት ነው . . . . . . . ጥቂት ዘይት ነው ያችኑ በልተን...ለነገ ደግም...አንተን ማየት ነው ግን አንተ ጌታ ምን ይሳንሃል የተራበን ነፍስ...አንተ አጥግበሃል

አዝ፡ አንተ እየመራኸን እዚህ ደርሰናል ክፉውን ዘመን በአንተ አልፈናል የነገውንም ደግሞ ታውቃለህ አንተ በታምራት...ታከርመናለህ...ታኖረናለህ (×፪)

መንገድህ ቁጭ አልኩ...ጭንቀት ቢይዘኝ . . . . . . . . ፈውስ ቢያምረኝ ከእውርነቴ...ብትፈታኝ ብዬ...ብትገላግለኝ አውቃለሁ ጌታ...ምን ይሳንሃል የእውሩን አይኖች...አንተ አብርተሃል

አዝ፡ አንተ እየመራኸን እዚህ ደርሰናል ክፉውን ዘመን በአንተ አልፈናል የነገውንም ደግሞ ታውቃለህ አንተ በታምራት...ታከርመናለህ...ታኖረናለህ (×፪)

ከባእድ ምድር...አንተ አወጣኸን...ለዚህ አደረስከን ወጉን ማዕረጉን...ባንተ ውስጥ ሆነን . . . . . . . ሁሉንም አየን ታዲያ ለነገ...ምን ያስፈራናል ኤልሻዳይ ጌታ...አንተ ካለኸን

አዝ፡ አንተ እየመራኸን እዚህ ደርሰናል ክፉውን ዘመን በአንተ አልፈናል የነገውንም ደግሞ ታውቃለህ አንተ በታምራት...ታከርመናለህ...ታኖረናለህ (×፪) }}