ኧረ ፡ እንዳንተ (Ere Endante) - ፌቨን ፡ ብርሃኑ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ፌቨን ፡ ብርሃኑ
(Feven Berhanu)

Feven Berhanu 1.jpg


(1)

በምህረትህ ፡ ተከልዬ
(Bemehereteh Tekeleyie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 4:38
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የፌቨን ፡ ብርሃኑ ፡ አልበሞች
(Albums by Feven Berhanu)

ኧረ ፡ እንዳንተ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ አለ
ኧረ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ፍቅር ፡ ልበልህ (፪x)

እናት ፡ እንኳን ፡ ልጇን ፡ ትረሳ ፡ ይሆናል
ጓደኛም ፡ ወዳጅም ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ ይከዳል
አንተ ፡ ግን ፡ አትከዳም ፡ ለዘለዓለም ፡ ነህ
ከእስትንፋሴ ፡ ይልቅ ፡ ለእኔ ፡ እጅግ ፡ ቅርብ ፡ ነህ

ኧረ ፡ እንዳንተ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ አለ
ኧረ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ፍቅር ፡ ልበልህ (፪x)

ከእናቴ ፡ ማህፀን ፡ ለራስህ ፡ የለየኸኝ
ከፊት ፡ እየቀደምክ ፡ እኔን ፡ የመራኸኝ
እጆቼን ፡ እየያዝክ ፡ ክፉን ፡ ያሳለፍከኝ
እግዚአብሔር ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ በእውነት ፡ የወደድከኝ

ፍቅር ፡ ቢባል ፡ እንዳንተ ፡ ማነው
ወዳጅ ፡ ቢባል ፡ እንዳንተ ፡ ማነው
አባት ፡ ቢባል ፡ እንዳንተ ፡ ማነው
ረዳት ፡ ቢባል ፡ እንዳንተ ፡ ማነው

አንተ ፡ ብቻ ፡ ለእኔ ፡ የቅርብ ፡ ወዳጄ
አንተ ፡ ብቻ ፡ ለእኔ ፡ የልብ ፡ ወዳጄ (፪x)

እንደ ፡ ሰው ፡ አይምሮ ፡ መቼ ፡ እኖራለሁ
ግን ፡ አንተ ፡ ይዘኸኝ ፡ ዛሬን ፡ አይቻለሁ
ለነገም ፡ አልፈራም ፡ በእጁ ፡ ውስጥ ፡ ነኝ
አመልካለሁ ፡ አንተን ፡ አባት ፡ ስለሆንከኝ

ፍቅር ፡ ቢባል ፡ እንዳንተ ፡ ማነው
ወዳጅ ፡ ቢባል ፡ እንዳንተ ፡ ማነው
አባት ፡ ቢባል ፡ እንዳንተ ፡ ማነው
ረዳት ፡ ቢባል ፡ እንዳንተ ፡ ማነው

አንተ ፡ ብቻ ፡ ለእኔ ፡ የቅርብ ፡ ወዳጄ
አንተ ፡ ብቻ ፡ ለእኔ ፡ የልብ ፡ ወዳጄ (፪x)

ኧረ ፡ እንዳንተ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ አለ
ኧረ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ፍቅር ፡ ልበልህ (፪x)