ቤዛ ፡ ሆነልን (Beza Honelen) - ፌቨን ፡ ብርሃኑ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ፌቨን ፡ ብርሃኑ
(Feven Berhanu)


(1)

በምህረትህ ፡ ተከልዬ
(Bemehereteh Tekeleyie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 8:25
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የፌቨን ፡ ብርሃኑ ፡ አልበሞች
(Albums by Feven Berhanu)

እንዲህ ፡ ተብሎ ፡ አይነገር ፡ የጌታ ፡ ምህረት
ለሰው ፡ ልጅ ፡ የሆነው ፡ ነገር ፡ በመስቀሉ ፡ ሞት (፪x)

ቤዛ ፡ ሆነልን ፡ በመሃል ፡ ገብቶ
ከሞት ፡ አዳነን ፡ ስለ ፡ እኛ ፡ ሞቶ (፪x)

በጎልጎታ ፡ የፈሰሰው ፡ ደሙ ፡ እኔን ፡ ለማዳን ፡ ነው
ፍቅሩን ፡ በሞት ፡ የገለጠው ፡ የታደገኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ፍቅሩን ፡ በሞት ፡ የገለጠው ፡ የታደገኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው

(እየሱስን ፡ ነው) ቤዛዬ ፡ ያልኩት
(እየሱስን ፡ ነው) ምትኬ ፡ ያልኩት
(እየሱስን ፡ ነው) ህይወቴ ፡ ያልኩት
(እየሱስን ፡ ነው) አዳኜ ፡ ያልኩት

በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሃጥያቴን
ተሸክሞ ፡ ሞተ ፡ ሞቴን
ዛሬ ፡ በህይወት ፡ የምኖረው
በሰራልኝ ፡ ውለታ ፡ ነው (፪x)

(እየሱስን ፡ ነው) ቤዛዬ ፡ ያልኩት
(እየሱስን ፡ ነው) ምትኬ ፡ ያልኩት
(እየሱስን ፡ ነው) ህይወቴ ፡ ያልኩት
(እየሱስን ፡ ነው) አዳኜ ፡ ያልኩት

አመልከዋለሁ ፡ ሁልጊዜ
ቤዛ ፡ ሆኗታል ፡ ለነፍሴ (፪x)
ኢየሱሴ ፡ አዳኝ ፡ ለነፍሴ
ኢየሱሴ ፡ ቤዛ ፡ ለነፍሴ
ኢየሱሴ ፡ አዳኝ ፡ ለነፍሴ
ኢየሱሴ ፡ ቤዛ ፡ ለነፍሴ

(እየሱስን ፡ ነው) ቤዛዬ ፡ ያልኩት
(እየሱስን ፡ ነው) ምትኬ ፡ ያልኩት
(እየሱስን ፡ ነው) ህይወቴ ፡ ያልኩት
(እየሱስን ፡ ነው) አዳኜ ፡ ያልኩት

የሃጢያት ፡ እዳ ፡ የከበደኝ
በጨለማ ፡ የተዋጥኩኝ
ሆኜ ፡ ሳለው ፡ እኔ ፡ እስረኛ
ኢየሱሴ ፡ ሞተልኛ
በርሱ ፡ መሞት ፡ ህያው ፡ ሆንኩኝ
ከዘላለም ፡ ጥፋት ፡ ዳንኩኝ

(እየሱስን ፡ ነው) ቤዛዬ ፡ ያልኩት
(እየሱስን ፡ ነው) ምትኬ ፡ ያልኩት
(እየሱስን ፡ ነው) ህይወቴ ፡ ያልኩት
(እየሱስን ፡ ነው) አዳኜ ፡ ያልኩት

ለምን ፡ እንደወደድከኝ ፡ ባይገባኝም
ይህንን ፡ አውቃለው ፡ ይህንን
ስለ ፡ እኔ ፡ ሞተህ ፡ በህይወት ፡ መኖሬ
ለዘለአለም ፡ ልጅህ ፡ መባሌ (፪x)

አይቻለው ፡ ምህረትህን
አይቻለው ፡ ልዩ ፡ ፍቅርህን
ማን ፡ እንዳንተ ፡ ይሆናል
ማንስ ፡ ልብን ፡ ይረዳል
ለእኔስ ፡ ሁሉን ፡ ሆንክልኝ
ጌታ ፡ በአንተ ፡ አማረብኝ (፪x)

ማዕረጌ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም
ትምክቴ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም
ጋሻዬ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም
ትምክቴ/ውበቴ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም (፪x)