From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
በምህረትህ ፡ ተከልዬ
አልፌአለው ፡ ሁሉን ፡ ችዬ
ስላለኸኝ ፡ ዋስትናዬ
ከቶ ፡ አልፈራም ፡ የነገዬን
በጨለመው(ባስጨናቂው) ፡ ሌሊት ፡ ያኔ ፡ አሳልፈኽ
ቀን ፡ ካወጣህልኝ ፡ እንባዬን ፡ አብሰኽ
ነገን ፡ እንዴት ፡ ልፍራ ፡ ልስጋ ፡ ለመኖሬ
አንተ ፡ እያለኸኝ ፡ የዘላለም ፡ ክብሬ
እንካ ፡ ምሥጋናዬን ፡ እንካ (፫x)
እንካ ፡ አምልኮዬን ፡ እንካ (፫x)
እንካ ፡ ሽብሸባዬን ፡ እንካ (፫x)
እንካ ፡ ዕልልታዬን ፡ እንካ (፫x)
ይገባሃልና ፡ ጌታ ፡ ይገባሃልና
ይገባሃልና ፡ ኢየሱስ ፡ ይገባሃልና
በምህረትህ ፡ ተከልዬ
አልፌአለው ፡ ሁሉን ፡ ችዬ
ስላለኸኝ ፡ ዋስትናዬ
ከቶ ፡ አልፈራም ፡ የነገዬን
ጠላት ፡ በዙሪያዬ ፡ ቢያገሳ ፡ እንዳንበሳ
ከለላዬን ፡ ሳይ ፡ ቢጮህ ፡ ቢያገሳ
የሰማዩ ፡ አባቴ ፡ እኔን ፡ ከልሎኛል
ክፉ ፡ አንዳያገኘኝ ፡ ቅጥር ፡ ቀጥሮልኛል
እንካ ፡ ምሥጋናዬን ፡ እንካ (፫x)
እንካ ፡ አምልኮዬን ፡ እንካ (፫x)
እንካ ፡ ሽብሸባዬን ፡ እንካ (፫x)
እንካ ፡ ዕልልታዬን ፡ እንካ (፫x)
ይገባሃልና ፡ ጌታ ፡ ይገባሃልና
ይገባሃልና ፡ ኢየሱስ ፡ ይገባሃልና
በምህረትህ ፡ ተከልዬ
አልፌአለው ፡ ሁሉን ፡ ችዬ
ስላለኸኝ ፡ ዋስትናዬ
ከቶ ፡ አልፈራም ፡ የነገዬን
ባሸናፊው ፡ ጌታ ፡ ሁሉን ፡ ነገር ፡ ጥዬ
በመንፈሱ ፡ ብርታት ፡ ቆምኩኝ ፡ ቀና ፡ ብዬ
በሃይሌ ፡ አይደለም ፡ ወይም ፡ በብርታቴ
ያቆመኝ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ የሆነኝ ፡ ጉልበቴ
እንካ ፡ ምሥጋናዬን ፡ እንካ (፫x)
እንካ ፡ አምልኮዬን ፡ እንካ (፫x)
እንካ ፡ ሽብሸባዬን ፡ እንካ (፫x)
እንካ ፡ ዕልልታዬን ፡ እንካ (፫x)
ይገባሃልና ፡ ጌታ ፡ ይገባሃልና
ይገባሃልና ፡ ኢየሱስ ፡ ይገባሃልና
በምህረትህ ፡ ተከልዬ
አልፌአለው ፡ ሁሉን ፡ ችዬ
ስላለኸኝ ፡ ዋስትናዬ
ከቶ ፡ አልፈራም ፡ የነገዬን
|