ይሳካል (Yesakal) - ፌበን ፡ ደምሴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ፌበን ፡ ደምሴ
(Feben Demissie)

Feben Demissie 1.jpg


(1)

ይሳካል
(Yesakal)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የፌበን ፡ ደምሴ ፡ አልበሞች
(Albums by Feben Demissie)

 
ህልመኛ ፡ ነኝ ፡ ህልም ፡ አለኝ ፡ የማያስቀምጠኝ
ባሳብኩት ፡ ቁጥር ፡ ውስጤን ፡ የሚያዘልለኝ
ለሌላው ፡ ባዋየው ፡ ቀድሞን ፡ ሁሌ ፡ ላይረዳኝ
ቀባጣሪ ፡ አስመሰለኝ ፡ ነገሬን ፡ ሲሰማኝ

ሁሁሁ ፡ አይ ፡ አይ (፪x)

እኖር ፡ ነበር ፡ በተከለለች ፡ ትንሽ ፡ ሜዳ
ትኩስ ፡ አየር ፡ ሲገባ ፡ ተሰማኝ ፡ በቅጥሩ ፡ ቀዳዳ
ተስፋ ፡ መልዕክት ፡ ይዞ ፡ ነው ፡ የመጣው ፡ ወደ ፡ እኔ
ሰብሬ ፡ የመውጣቴ ፡ ዛሬ ፡ ነው ፡ ቀኔ

ሁሁሁ ፡ አይ ፡ አይ (፪x)

(ማነው ፡ ያለው) አይሳካልሽም
(ማነው ፡ ያለው) መድረሻ ፡ የለሽም
(ማነው ፡ ያለው) ፍሬያማ ፡ አትሆኝም
(ማነው ፡ ያለው) ለሌላው ፡ አተርፊም

ይሳካል ፡ ይሆናል (፫x)

ለሚያምን ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል (፫x)
ምንም ፡ የሚያቅተኝ ፡ የለም ፡ ለእኔ
ለሚያምን ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል (፫x)
ምንም ፡ የሚያቅተኝ ፡ የለም ፡ ለእኔ

እንደ ፡ ንስር ፡ ክንፍ ፡ አውጥቼ???
እበራለሁ ፡ የኋላዬን ፡ ትቼ
እበራለሁ ፡ የኋላዬን ፡ ትቼ
ምንም ፡ የሚያቅተኝ ፡ የለም ፡ ለእኔ (፫x)
ምንም ፡ የሚያቅተኝ ፡ የለም ፡ ለእኔ

(ማነው ፡ ያለው) አይሳካልሽም
(ማነው ፡ ያለው) መድረሻ ፡ የለሽም
(ማነው ፡ ያለው) ፍሬያማ ፡ አትሆኝም
(ማነው ፡ ያለው) ለሌላው ፡ አተርፊም (፪x)