ትልቅን ፡ ነገር ፡ አስባለሁ (Teleqen Neger Asebalehu) - ፌበን ፡ ደምሴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ፌበን ፡ ደምሴ
(Feben Demissie)

Feben Demissie 1.jpg


(1)

ይሳካል
(Yesakal)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የፌበን ፡ ደምሴ ፡ አልበሞች
(Albums by Feben Demissie)

 
በማዘን ፡ መተከዝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይከብር ፡ ይመስል
ምንድን ፡ ነው ፡ መርበትበት ፡ ሁልጊዜ ፡ መቆዘም
ጠላት ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ በዚያ ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ የሚለው
ምን ፡ ይጨምራል ፡ የአምላክን ፡ ሃይል ፡ መጠርጠር ፡ ነው

አዝ፦ አላንጐራጉርም ፡ አንገቴንም ፡ አልደፋም
እግዚአብሔር ፡ እንቅቶኛል ፡ ጊዜዬን ፡ አላጠፋም (፪x)

ምን ፡ አሸማቀቀኝ ፡ ምን ፡ አንገቴን ፡ አስደፋኝ
ጌታዬ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ሆኖ ፡ እያየሁኝ
የማልፍበት ፡ ሁሉ ፡ እንደምናምን ፡ ቢመስልም
ነጥሬ ፡ እወጣለሁ ፡ ወደኋላዬ ፡ አልልም

አዝ፦ አላንጐራጉርም ፡ አንገቴንም ፡ አልደፋም
እግዚአብሔር ፡ እንቅቶኛል ፡ ጊዜዬን ፡ አላጠፋም (፪x)

የትም ፡ ስፍራ ፡ ብሆን ፡ የሚይዘኝ ፡ ምንም ፡ የለም
እሰራለሁ ፡ ስራ ፡ አለኝ ፡ ገና ፡ ያልጀመርኩት
ሲያየኝ ፡ ጠላቴ ፡ ለዐይኑ ፡ ባልሞላለትም
እግሬ ፡ የረገጠበት ፡ ሰላም ፡ አልሰጠውም

አዝ፦ አላንጐራጉርም ፡ አንገቴንም ፡ አልደፋም
እግዚአብሔር ፡ እንቅቶኛል ፡ ጊዜዬን ፡ አላጠፋም (፪x)

የደከምኩ ፡ ስመስለው ፡ አሳድደዋለሁ
ተኛታለች ፡ ብሎ ፡ ሲል ፡ ህልምን ፡ አልማለሁ
ዛሬ ፡ አዘነች ፡ ሲል ፡ እዘምራለሁ
ከአምላኬ ፡ ተጣብቄ ፡ ግራ ፡ አጋባዋለሁ

አዝ፦ አላንጐራጉርም ፡ አንገቴንም ፡ አልደፋም
እግዚአብሔር ፡ እንቅቶኛል ፡ ጊዜዬን ፡ አላጠፋም (፪x)

ትልቅን ፡ ትልቅን ፡ ነገርን ፡ ሁልጊዜ
አስባለሁ ፡ አምላኬ ፡ ያንኑ ፡ ሲያደርግ ፡ አየዋለሁ
ከፍ ፡ ያለውን ፡ ከፍ ፡ ያለውን ፡ ነገርን ፡ ሁልጊዜ
አስባለሁ ፡ አምላኬ ፡ ያንኑ ፡ ሲያደርግ ፡ አየዋለሁ (፬x)